ዜናፖለቲካ

ዜና: ጠ/ሚኒስትር አብይ በአማራ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ 6ሺ የሚጠጉ ሱዳናውያንን እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበላቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል “ከአውላላ የስደተኞች መጠለያ” ወጥተው በአቅራቢያው በሚገኝ መንገድ ዳር መኖር የጀመሩ ስድስት ሺ የሚሆኑ የሱዳናውያን ስደተኞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በመሆናቸው እንዲታደጓቸው የሱዳን ድርጅቶች ለጠ/ሚኒስትር አብይ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

ከግንቦት ወር መባቻ ጀምሮ በአማራ ክልል ከሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የጸጥታ ችግር አጋጥሞናል በሚል ካምፑን ለቀው በመውጣት በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጫካ ውስጥ መኖር የጀመሩ ስድስት ሺ የሚጠጉ ሱዳናውያን መኖራቸውን ድርጅቶቹ ጠቁመዋል።

በአስከፊ ሰብአዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ ማለታቸውንም ሚድል ኢስት ሞኒተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ስድስት ሺ ከሚሆኑት እና በጫካው ውስጥ ከሚኖሩት ሱዳናውያኑ መካከል 2 ሺ 133 የሚሆናት ህጻናት መሆናቸውን የጠቆሙት ድርጅቶቹ 1 ሺ 17 የሚሆኑት ሴቶች፣ 1 ሺ 917 ወንዶች፣ 1 ሺ 135 የሚሆኑ በሽተኞች እና 76 የሚሆኑት ደግሞ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ናቸው ብለዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ (ኦቻ) እና ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ሱዳናውያኑ ስደተኞች ያሉባቸውን ችግሮች እንዲገነዘቡላቸው እና አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።

በጫካ ውስጥ በመኖር ላይ ያሉት ሱዳናውያን 22 ቀናት አስቆጥረዋል ብለዋል። የምግብ እና መድሃኒት ጨርሰዋል ሲሉ አሳስበዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ሱዳናውያን ስደተኞች ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከመጠለያ ካምፑ በመውጣት በመንገድ ዳር ላይ የሚገኙትን ስደተኞች ለማገዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን የጠቆመው ኮሚሽኑ በተመሳሳይ የአከባቢው ባለስልጣናት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጥበቃ እያደረጉላቸው መሆኑን አስታውቋል።

በአከባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ እጅግ አስጊ እና ፈታኝ መሆኑን በመጠቆም ከአውላላ የስደተኞች መጠለያ አቅራቢያ ባለፈው ሳምንት አርብ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም የረድኤት ሠራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰራተኛ መገደሉን በማሳያነት ጠቅሷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button