ማህበራዊ ጉዳይዜናፖለቲካ

ዜና: የመንግስታቱ ድርጅት በኢትዮጵያ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋ ሲል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው ተፈናቅለው ከነበሩ ዜጎች መካከል ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀ።

አብዘሃኛዎቹ (65 በመቶ የሚሆኑት) ከቀያቸው የመፈናቀላቸው ምክንያት በአከባቢያቸው የተከሰተው ጦርነት እና ግጭት ነበር ሲል የገለጸው ሪፖርቱ 18 በመቶ የሚሆኑት ግን በአከባቢያቸው በተከሰተ ድርቅ ሳቢያ ተፈናቅለው የነበሩ ናቸው ብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ባወጣው ሪፖርት ወደ ቀያቸው ከተመለሱት ውጭ በሀገሪቱ በአጠቃላይ ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮች አሁንም አሉ ብሏል።

በሀገሪቱ ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ተፈናቃይ የሚገኘው በሶማሌ ክልል ነው ሲል የገለጸው የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች አሉ ብሏል።

እንደ መንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ከሆነ በኦሮምያ ክልል ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊየን 64ሺ ሲሆን፤ ከትግራይ ክልል ደግሞ አንድ ሚሊየን 21ሺ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ይገኛሉ ሲል አስታውቋል።

በመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት መሰረት ከአማራ ክልል ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 436ሺ 805 መሆኑን አመላክቷል።

አብዘሃኛዎቹ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙባቸው ክልሎችም ሶማሌ (1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ) ፣ ኦሮምያ (ከአንድ ሚሊየን በላይ) እና ትግራይ (ከአንድ ሚሊየን በላይ) ናቸው ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የመንግስታቱ ድርጅት እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቀያቸው ከተመለሱ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች መካከል በትግራይ 967ሺ 257 ሰዎች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል ሲል ገልጿል፤ አሁንም ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች ግን አሁንም እንደተፈናቀሉ ናቸው ብሏል።

በኦሮምያ ክልል ወደ ቀያቸው የተመለሱ ሰዎች ቁጥር 137ሺ 230 ይሆናሉ ያለው ሪፖርቱ አሁንም ከአንድ ሚሊየን በላይ እንደተፈናቀሉ ናቸው፣ አልተመለሱም ብሏል።

በአማራ ክልል ከቀያቸው ተፈናቅለው ከነበሩ ሰዎች መካከል 951ሺ 931 ሰዎች ተመልሰዋል ሲል የገለጸው ሪፖርቱ አሁንም 436ሺ 805 ነዋሪዎች እንደተፈናቀሉ ናቸው ብሏል።

የመንግስታቱ ድርጅት በሪፖርቱ አንድ ሚሊየን 64ሺ የሚሆኑ ከሌሎች ሀገራት ተሰደው በኢትዮጵያ የተጠለሉ እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መኖራቸውን አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button