ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና፡ የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ከእስር ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2/ 2016 ዓ/ም፡– “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ትላንት ሰኔ 1/ 2016 ከእስር መፈታታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ገለጹ።

አቶ የሺዋስ ታመው ስለነበር እንደተፈቱ ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኘው መቅረዝ ሆስፒታል በማምራት ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቢቤታቸው ገብለዋል ሲሉ ወ/ሮ ሙሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። 

አርብ ግንቦት 23 ቀን በፖሊስ ቁጥጥር የዋሉት አቶ የሺዋስ “ሚዲያን በመጠቀም ሰው እንደነሳሳ አድርገሃል” በሚለ መጠርጠራቸው በቃል እንደተነገራቸው ባለቤታቸው ገልጸዋል። 

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ /ኢሕአፓ/ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት የሺዋስ ከእስር የተፈቱት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲሁም በዋስትናም እይደለም ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። 

አክለውም፣ ህዳር 30 ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ አፋር በሚገኘው አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የነበሩ ሰባት ፖለቲከኞችም እርብ ዕለት ወደ አዲስ አበባ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወራቸውን አብርሃም ሃይማኖት ተናግረዋል። 

የኢሕአፓ ሊቀንመር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ ውደ አዲስ አበባ መዘዋወራቸው የተገለጸውን ፖለቲከኞች ከቤተሰብ ጋር እየተገናኙ አለመሆኑን የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ገልጸዋል።

“ፖለቲከኞቹ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጭለማ ቤት እየተሰቃዩ ነው” ያለት መጋቢ ብሉይ አብርሃም  “ድርጊቱን እየፈጸሙ ያሉ የመንግስት አካላት ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ” አሳስበዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ኅዳር 30 የተጠራው ሰልፍ አስተባባሪ የነበሩት አቶ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ ባሳለፍነው ሳምንት ግንቦት 28 ቀን 2016 መሳለሚያ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተይዘው መታሰራቸውን አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button