የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ “ሁከት በማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን የቤተሰብ አባል ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27/2016ዓ/ም:- የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ “ሁከት በማነሳሳት” ተጠርጥረው አርብ ግንቦት 23 ቀን በፖሊስ ቁጥጥር መዋላቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ።

የፖለቲከኛው ባለቤት ወ/ሮ ሙሉ “ሲቪል የለበሱ የፖሊስ አባላት አርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት ወደ መኖሪያ ቤታችን በመምጣት ለጥያቄ እንፈልግሃል በሚል ይዘውት ሂደዋል” ሲሉ ክስተቱን አስረድተዋል።

ፖሊሶቹ አቶ የሺዋስን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ያል ፍርድ ቤት ማዘጃ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።

በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ የሺዋስ በትላንትናው ዕለት “ሚዲያን በመጠቀም ሰው እንደነሳሳ አድርገሃል” በሚል መጠርጠራቸውን ፖሊስ መግለፁን ባለቤቱ ተናግረዋል።

አቶ የሺዋስም ሚዲያ የሌላቸው መሆንን ለፖሊስ ገልፀው “የለኝም ብለህ ፈርም” ተብለው መፈረማቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ወ/ሮ ሙሉ አስረድተዋል።

በማግስቱም ፖሊሶች የሺዋስን ወደ መኖሪያ ቤቱ የዘውት በመሄድ ፍተሻ ማድረጋቸውን እና ምንም ነገር ሳያገኙ መመለሳቸውን አክለው ገልጸዋል።

አቶ የሺዋስ ከሌሎች ፖለቲከኞች ጋር በመሆን “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር  የሚታወስ ነው።

ነገር ገን “በመንግስት ጫና ምክንያት” ሰልፉ ሳይከናወን መቅረቱን የሰልፉ አስተባባሪዎቹ
በወቅቱ ገልፀዋል። በተጠራው ሰልፍ መክንያት አራት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት መታሰራቸውንም ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ስራ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ የሺዋስ ባሳለፍነው አመት በገዛ ፍቃዳቸው  ከሌሎች የፓርቲው አባሎች ጋር በመሆን ከፓርቲው አባልነት መልቀቃቸው ይታወቃል። አስ

Exit mobile version