ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት “ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አለው” በሚል የቀረበበትን ውንጀላ አስተባበለ

“በኮርያውያኑ እገታ እጄ የለበትም” ሲል ገልጿል።

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 17/ 2016 ዓ/ም፦ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከሶማሊያው “አልሸባብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው” ሲል የኢትዮጵያ  ብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መወንጀሉን ቡድኑ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ “ከአልሸባብ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም” ሲል አስተባብሏል።

የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የመረጃ ተቋማት ሃላፊዎች በአዲስ አበባ ያካሄዱትን ውይይት ተከትሎ አገልግሎቱ ለመገናኛ ብዙኃን በለከው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት “በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር እና በኬኒያ ውስጥ “ዜጎችን የማገት፤ ንብረት የመዝረፍ የማውደምና እንዲሁም የሰዎችን እንቅስቃሴ የማስተጓጎል” ስራዎች እየሰራ ነው ሲል ከሷል።  

የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አክሎም ቡድኑ “ከአልሸባብ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አለው” ሲል ገልጾ፤ “ሁለት የኮርያ ዜጎችን በማገት ለአልሸባብ አሳልፎ ሠጥቷል” ብሏል። 

በተጨማሪም ቡድኑ “የኮንትሮባንድ ንግድ፤ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፤ ህገወጥ የማዕድን ማውጣትና ማዘዋወር” ስራዎች ላይ መሰማራቱን ጠቁሞ፤ ይህንንም ለማስቆም የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የመረጃ ተቋማት አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ገልጿል።

ስክሱን ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ትላንት ነሃሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “አልሸባብ ሙስሊሞች በብዛት የሚኖሩባቸውን የኦሮሚያ ክልል ግዛቶች የሱማሊያ ግዛት አድርጎ እንደሚቆጥር” ጠቁሞ  “የትኛውም የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይል ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ሊመሠርት አይችልም” ሲል ገልጿል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት “በኮርያውያኑ እገታ እጄ የለበትም” ሲል በማስተባበል “በኮሪያዊያኑ አፈና ዙሪያ የገለልተኛ ምርመራ ውጤት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ” ገልጾ “ተላልፈው ለአልሸባብ የተሰጡት በኢትዮጵያ መንግስት ሊሆን ይችላል” ሲል መላምቱን አስቀምጧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ አማካኝነት ከሶማሊያ ጋር ለሚያደርገው ድርድር ጉልበት እንዲሆነው እና ለሶማሊያ መንግስት መልዕክት ለማስተላለፍ ሲል የፈጸመው ተግባር ሊሆን ይችላል” ሲል ገልጿል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button