ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ኦብነግ የኢትዮጵያ መንግስት “ሕገ-መንግስታዊ መብትን እና የሰላም ስምምነትን ጥሷል" ሲል ከሰሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8/ 2017 ዓ/ም፦ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሶማሌ ክልል የወሰዱት እርምጃ “ህገ መንግስታዊ መብቶችን” እና “ በፈረንጆቹ 2018 በኦብነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት” የሚጥስ ነው ሲል እንዳሳሰበው ገልጿል። 

ኦብነግ ዛሬ መስከረም 8/2016ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፤ “የሶማሌ ሽማግሌዎች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማህበረሰብ አባላት በቴሌቭዥን ቀርበው የሶማሌ ማንነታቸውን በመካድ ራሳቸውን እንዲያዋርዱ ተደርገዋል” ብሏል።

በተጨማሪም ድርጅቱ፤ “የሶማሌ ክልል ስም እና ሰንደቅአላማ ሊቀየር ነው የሚል አስደንጋጭ ጭምጭምታ” ሰምቻለሁ ሲል አስታውቋል።

ኦብነግ መግለጫውን ያወጣው በቅርቡ የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች “ሶማሊያውያን የራሳቸው ያልሆነ ጦርነትን ወደ ሀገራቸው ከመጋበዝ እንዲቆጠቡ” ማሳሰባቸውን ተከትሎ ነው። 

እንደ ኦብነግ መግለጫ፤  እነዚህ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ያሉት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ ባለበት ወቅት ነው።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)  በ”ሶማሌ ክልል ያለው ሁኔታ ወታደራዊ መልክ እያያዘ እና ክልሉ በወታደራዊ አስተዳደር ሊወድቅ ይችላል።” ሲል አስጠንቅቋል።

ፓርቲው በመግለጫው በኢትዮጵያን ሕገ መንግስት አንቀጽ 39 ስር የተደነገገውን ማንኛውም ብሔር ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን በመጠቀስ፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለሁሉም ዜጎቹ የእኩልነት መርህን ማስከበር አለበት” ሲል አሳስቧል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ የጠየቀው ፓርቲው፤ “የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሌን ህዝብ ሕገ-መንግስታዊ መብት እና የሰላም ስምምነቱን እንዲያከብር” አሳስቧል።

ድርጅቱ ይህን አለማድረግ “ለተጨማሪ አለምረጋጋት ስጋት መሆኑን እና የክልሉን ሰላም አደጋ ውስጥ የሚከት ነው“  ሲል ገልጿል።

ባሳለፍነው ሳምንት ኦብነግ ባወጣው መግለጫ፤  የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፓርቲውን በተመለከተ አድርገዋል የተባለውን ንግግር “የሰላም ስምምነትን የሚጥስ” ሲል መቃወሙ ይታወሳል።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ባወጣው መግለጫ፤ በጷጉሜ 3/2016 ዓ.ም. በኢትዮ ፎረም ሚዲያ በተሠራጨው ቪዲዮ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ፓርቲውን “በግብጽ የተፈጠረ የኢትዮጵያ ጠላት” ሲሉ ተደምጠዋል ብሏል።

የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አድርገዋል የተባለውን ንግግር “ቀስቃሽ” ሲል የተቃወመው ኦብነግ፣ “መሠረተ ቢስ” እና “በሕጋዊነቱ ላይ የተቃጣ” ሲልም ፈርጇል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button