ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በአማራ ክልል የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት የገና እና የጥምቀት በዓላት ሚና ይኖራቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25/2016 .ም፡ የገና እና ጥምቀት በዓላት በአማራ ክልል የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት የሚያስችሉ መሆኑን የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

በሀገሪቱ የገና እና ጥምቀት በዓላት በድምቀት ከሚከበርባቸው አካባቢዎች አማራ ክልል በቀደምትነት ይጠቀሳል ሲሉ የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢአለ መግለጻቸውን ያስነበበው ኢፕድ እነዚህ በዓላት በክልሉ ተቀዛቅዞ የቆየውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት የሚያችሉ በመሆናቸው በትኩረት እየተሠራ ነው ሲሉ መናገራቸውን አስታውቋል።

በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት የከተማው ምጣኔ ሀብት ከፍተኛ መቀዛቀዝ አሳይቷል ሲሉ አቶ አበበ ገልጸዋል ያለው ዘገባው ሁለቱን በዓላት በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ክልሉን ብሎም ሀገሪቱ ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ በደመቀ ሁኔታ ለማክበርም የዝግጅት ሥራዎችን እየተሠሩ ነው ማለታቸውንም አመላክቷል።

ዘንድሮ በታኅሣሥ 28 የሚከበረውን የገና በዓል በላሊበላ ከተማ ለማክበር የከተማው አስተዳደር ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደርና የቱሪዝም ቢሮ ከክልሉ ጋር በመሆን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይም በደመቀ መልኩ በጎንደር የሚከበረው የጥምቀት በዓል እንደክልል ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ ባለፈው ዓመት በሁለቱ በዓላት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በእያንዳንዳቸው ላይ የተገኘ መሆኑን አቶ አበበ አስታውሰዋል ብሏል። በዚህ ዓመትም ተመሳሳይ መልኩ በደመቀ መልኩ ለማክበር እና ቀጣይነት እንዲኖረውን ይሠራል ማለታቸውን አካቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገና እና ጥምቀትን በዓላትን ታሳቢ በማድረግ በክብረ በዓሉ ለመታደም የሚመጡ ጎብኚዎች ከባሕርዳር ላሊበላ እና ከጎንደር ላሊበላ ለመንቀሳቀስ በቀጥታ የአየር ትራንስፖርት መፍቀዱንም ገልጸዋል ያለው ዘገባው በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ፓኬጁን ቁጥርን እንዲጨምር ለማድረግ የክልሉና ፌዴራል ቱሪዝም ቢሮ እየሠራ ነው ማለታቸውንም ጠቁሟል።

በክልሉ የሚገኙ ሆቴሎች፣ ትራንስፖርት፣ አስጎብኚ ማኅበራትና መሰል አገልግሎት ሰጪዎች ጋር በጋራ እየተዘጋጁ መሆኑን አቶ አበበ ገልጸዋል ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሄዱ ያሉ ግጭቶች እና አለመርጋጋቶች የቱሪዝም ዘርፉ ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀናቸውን የተመለከተ ትንታኔ ማስነበባችን ይታወሳል።

በትንታኔው በቱሪስት መስህብነቱ የበረካታ ጎብኚውችን ልብ የመሳብ አቅም ያለው አማራ ክልል በግጭት ምክንያት በክልሉ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትጽዕኖ እያደረሰ መሆኑን በክልሉ በአስጎብኚነት ስራ ላይ ተሰማረቶ የሚገኝ ባለሙያ ለአዲስ ስታንዳርድ መግለጹ ተካቷል።

ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው አስጎብኚው “በክልሉ በተቀሰቀሰው ግጭት እና የእንቀሰቃሴ ገደብ በመኖሩ ምክንያት ወደ ከልሉ የሚመጡ ጎብኚዎች የሉም” ሲል ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል። በዚህም የተነሳ በዘረፉ ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ ተጽዕኖ እየደረስ መሆኑን አስጎብኚው ጠቅሷል። “ ከጦርነቱ በኋላ ትንሽ መነቃቃት ነበር አሁን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የቱሪዝም ዘርፉ ቆሟል፤ ሰላም እስኪውርድ ቁጭ ብለን እየተበቀን ነው” ሲል በክልሉ ያለውን የቱሪዘም ዘረፉን መዳከም ገልጿል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button