ዜናፖለቲካ

ዜና፡ አለም አቀፍ የኦሮሞ ቤተ እምነቶች ምክር ቤት በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካካል የሰላም ድርድር እንዲቀጥል ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14/ 2016 ዓ/ም፦ ተውፊቅ ኢስላማዊ ማዕከል፣ የኦሮሞ አንድነት ኢቫንጄሊካል ቤተ ክርስቲያንን ጨመሮ በስሩ አስራ አራት ቤተ እምነቶችን አቅፎ የያዘው አለም አቀፍ የኦሮሞ ቤተ እምነቶች ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህምድ( ዶ/ር) እና ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት(ኦ.ነ.ሰ)  ዋና አዛዥ ኩምሳ ዲሪባ( ጃል መሮ) በጻፈው ደበዳቤ በመንግስት እና በኦነስ መካከል ሳይውል ሳያድር ቀጣይ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ጠየቀ፡፡ 

ምክር ቤቱ የፌዴራሉ መንግስትና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በታነዛኒያ ዳሬስላም ሲያካሄዱት የነበረው የሰላም ድርድር ለሁለተኛ ግዜ ያለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ በጻፈው ደብዳቤ “ውስብስብ የሆኑ ችግሮች እና የግዜ እጥረቱን እንገነዘባልን፤ ይሁን እንጂ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ግጭትን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንድትቀጥሉ እንጥይቃለን”ብሏል።

ሁለቱም ወገኖች በመካከላቸው ለተፈጠረው ልዩነት ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት በድጋሜ ውይይት እንዲካሄድ ያሳሰበው አለም አቀፍ የኦሮሞ ቤተ እምነቶች ምክር ቤት በሁለተኛው ዙር ድርድር ጥሩ ውጤት ይገኛል ተብሎ ቢጠበቅም ባለመሳካቱ መዘኑን ገልጿል።

በተጨማሪም፣ በዚህ ታሪካዊ እድል በመጠቀም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በቁረጠኝነት እንዲሰሩ በደብዳቤው የጠየቀው ምክር ቤቱ፣ “በህዝቡ ታሪከ በዚህ ወሳኝ ወቅት በመረዳት የተሞላ እና ገንቢ በሆነ ውይይት ስላምን መሻትና ባለው እሴት ከመጠቀም በላይ ወሳኝ ነገር የለም” ብሏል።

ምክር ቤቱ በሁለቱ አካላት መካከል ለረጅም አመት በቆየው አለመግባባት የተነሳ በመካከላቸው ጥረጣሬ መፈጠሩን በመጠቆም የተፈጠረውን ጥርጣሬ በማጠፋት ለሀዘቡ ጥቅም እንዲሰሩ አሳስቧል። አክሎም ጥርጣሬን በማስወገድ መተማመንን በመፍጥር የጋራ ጉዳይ ላይ እንዲያቶክሩ ጠይቋል።

ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከንብረታቸው ተፈናቅለው በረሃብና በበሽታ የሚሞቱ ዜጎችን ችግር በመንገንዘብ ሁለቱም ወገኖች ለሰላም ሊሰሩ እንደሚገባም ተጠቁሟል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button