ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢሰመኮ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት፣ በከባድ መሣሪያ እና ድሮን የታገዘ መሆኑን፣ 200 የሚደርሱ ሴቶች መደፈራቸውን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19/2016 .ም፡ በአማራ ክልል ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ በከባድ መሣሪያ እና ድሮን ድብደባ የታገዘ የትጥቅ ግጭት እንደተካሄደባቸው እና በግጭቱም ንጹሃን የክልሉ ነዋሪዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ።

በአማራ ክልል የሚገኙ ወረዳዎች በአንድ ወቅት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በሌላ ወቅት በታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) ቁጥጥር ሥር ውለዋል ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የትጥቅ ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር/ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ መሆኑን አስታውቋል።

ኢሰመኮ በመግለጫው ካካተታቸው ጉዳዮች መካከል 200 የሚደርሱ አስገድዶ መድፈር የተፈጸመባቸው የክልሉ ሴቶች ይገኝበታል። ኮሚሽኑ በመግለጫው በግጭቱ አውድ የሚፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች በጣም አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ተገቢው ምርመራ ተደረጎ እርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው መሆኑን ጠቁሞ  የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት በተለያዩ የጤና ተቋማት መድረስ የቻሉትን ተጎጂዎች ቁጥር ብቻ መሠረት በማድረግ፣ ከሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ቢያንስ 200 የአስገድዶ መድፈር ተጎጂዎች በጤና ተቋማት መመዝገባቸውን በተለይም ከመንግሥት ተቋማት ጭምር የደረሱትን መረጃዎች ዋቢ በማድረግ አስታውቋል፤ ከተጎጂዎች መካከልም የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሴቶች እና የጤና ባለሞያ ሴቶች ጭምር እንደሚገኙበት ጠቁሟል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ጥቃትን አልያም ግጭትን በመሸሽ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ከቀያቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ መቻሉን መግለጫው አካቷል።

የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት ከህግ ውጭ ግድያዎች እየፈጸሙ መሆኑን ያመላከተው የኢሰመኮ መግለጫ ግድያው የተፈጸመው በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ የያዟቸውን መሆኑን ገልጿል፤ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፣ ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ፣ መሣሪያ አምጡ፣ የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ” በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ተዓማኒ መረጃዎች ለኮሚሽኑ ደርሰውታል ብሏል።

በክልሉ በገንዘብ ዝውውር ላይ ገደብ መጣሉን ያመላከተው መግለጫው በአንዳንድ ተቋማት የደመወዝ ክፍያ መቋረጥም ነዋሪዎችን ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መዳረጉን ገልጿል።

በክልሉ በተለየ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው ተቋማት በስተቀር የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የጠቆመው ኢሰመኮ በተለይም በግጭት ላይ ባሉ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎትም ጨምሮ መቋረጡን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ኢሰማኮ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል ሲል ጠይቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button