ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር በኩል የወደብ ባለቤት ለመሆን ለጎረቤቶቿ ያቀረበችውን ጥያቄ ጅቡቲ ውድቅ ማድረጓ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8/2016 .ም፡ ጅቡቲ ኢትዮጵያ በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት ለጎረቤት ሀገራት በቅርቡ ያቀረበችውን የወደብ ባለቤትነት ድርድር እንደማትቀበለው መግለጿን ብሉንበርግ አስታውቋል። ጅቡቲ ከኤርትራን እና ሶማሊያ በመቀጠል የኢትዮጵያን ጥያቄ ውድቅ ያደረገች ሶስተኛ ሀገር ሁናለች።

ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ጠንካራ የሆነውን ግንኙበታቸውን አስጠብቀው የሚኖሩ ሀገራት ናቸው፤ ነገር ግን ጅቡቲ ሉአላዊ ሀገር ናት የግዛት አንድነታችን ዛሬም ሆነ ወደፊት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጊሌ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አሌክሴስ ሞሃመድ መናገራቸውን እና በሀገራቸው በኩል ጥያቄው ተቀባይነት እንደሌለው መግለጻቸውን ብሉንበርግ ባስነበበው ዘገባው አስታውቋል።

የጂቡቲ ምለሽ ከመገለጹ በፊት ሶማሊያ ከኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረበላት የወደብ ባለቤትነት ውይይት እንደማትቀበለው ማስታወቋን ብሉንበርግ በድረገጹ ማስነበቡ ይታወሳል። የኢትዮጵያን ጥያቄ እንደማትቀበለው እና የወደብ ጉዳይ ልክ እንደ ሌሎች የሉኣላዊነት ጉዳዮች የሚታይ ነው ማለቷን ዘገባው አካቷል።

በተጨማሪም የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አማካሪ አብዲራህማን አብዲሻኩር በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በኩል በተደጋጋሚ የወደብ ባለቤትነትን አስመልክተው የሚሰጡትን አስተያየት እንዲሁ ችላ የምንለው አይደለም ሲሉ መግለጻቸውንም ሶማሊ ጋርድያን በድረገጹ አስነብቧል። መንግስታቸው ሁኔታውን በትኩረት እንዲከታተለው ማሳሰባቸውንም አስታውቋል።

የሶማሊያ ብሔራዊ የደህንነት መስሪያ ቤት (NISA) ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት ኢስማኤል ኦስማን በዩሮኤዥያ ሪቪዩ ድረገጽ ባሰፈሩት ጽሁፍ ኢትዮጵያ በቀይባህር ዙሪያ የወደብ ባለቤት ለመሆን እየሄደችበት ያለው መንገድ አለምአቀፍ አካሄድን የጣሰ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ኢስማኤል ኦስማን በድረገጹ ባሰፈሩት ትንታኔ የአለም ሀገራት የራሳቸው የሆነ በርካታ የተፈጥሮ ሀብት እንዳላቸው ጠቁመው ሀገራት ይህንን የተፈጥሮ ሀብት ማለትም ነዳጅም ሆነ ወደብ በአለም አቀፍ የትብብር እና በሰላማዊ መንገድ በሽያጭ እና በተለያየ መንገድ በጋራ እንደሚጠቀሙ አስታውቀዋል። ከዚህ ውጭ ግን በጉልበት ለማግኘት መጣር አለምአቀፍ አካሄድን የጣሰ ነው ሲሉ ተችተዋል። ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቀይባህር ዙሪያ የወደብ ባለቤት ለመሆን ያቀረቡት ሀሳብ እና ለማግኛነት ያቀረቡት አካሄድ የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን እና አለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የአለም አቀፉ የዲፕሎማሲ ውበት ሀገራት የሌላቸውን እና በሌሎች ሀገራት ላይ ያለን ሀብት እና ጥንካሬ እውቅና በመስጠት በትብብር ለመጠቀም የሚደረግ ጥረት ነው ያሉት የቀድሞ የሶማሊያ የስለላ ተቋም ምክትል ዳይሬክተሩ ጉልበት በተላበሰ መንገድ የሌሎችን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠቀም መጣር ደካማነት ነው ሲሉ ኮንነዋል።

ሌላኛው የቀድሞ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ባላል ሞሃመድ ኩስማን በበኩላቸው የጠ/ሚኒስትሩ የወደብ ባለቤትነት ሀሳብ ኢትዮጵያ ከአጎራባቾቿ ጋር ያለትን የቆየ ቁርሾ እንደመቀስቀስ ይቆጠራል ሲሉ ተችተዋል። ባላል ሞሃመድ ሂራን ድረገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ጠ/ሚኒስትር አብይ ዛይላ ወደብን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት በብዙ ጥረት ወደ መልካም ግንኙነት የተመለሰውን የሶማሊያ እና ኢትዮጵያን ግንኙነት በሚያበላሽ ነው ሲሉ አሳስበዋል። ጉዳዩ ቀጠናውን ወደ ቀውስ የሚወስድ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከሶማሊያ ቀደም ብላ ኤርትራ በማስታወቂያ ሚኒስትሯ በኩል የኢትዮጵያን ጥያቄ እንደማትቀበለው እና ቦታ እንደማትሰጠው መግለጿም ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button