ቢዝነስዜና

ዜና፡ ኢትዮጵያ በተያዘው አመት ለጎረቤት ሀገራት ሶስት ሺ የሚጠጋ ጊጋዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ለሽያጭ ለማቅረብ ማቀዷን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5/2016 .ም፡ ኢትዮጵያ በተያዘው የበጀት አመት 2016 ለሶስት የጎረቤት ሀገራት ማለትም ለሱዳን፤ ለኬንያ እና ለጅቡቲ ሶስት ሺ የሚጠጋ ጊጋ ዋት አዎር የኤሌክትሪክ ኃይል ለሽያጭ ለማቅረብ ማቀዷን አስታወቀች።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ሀገሪቱ ለጎረቤቶቿ ለመሸጥ ካቀረበችው የኤሌክትሪክ ሀይል 182 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት እየሰራች መሆኑን አመላክተዋል።

ባለፈው በጀት አመት ለሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ አንድ ሺህ 701 ጊጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት መደረጉን አቶ ሞገስ ጠቁመዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይልን ለውጭ ሀገራት ኤክስፖርት በማድረግ የሀገሪቷን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለማሳደግ አዳዲስ ስምምነቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ሞገስ ስምምነቶቹ በተያዘላቸው ቀነ ገደብ የሚጠናቀቁ ከሆነ በዘንድሮው በጀት ዓመት ወደ ታንዛኒያ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ይደረጋል ሲሉ መግለጻቸውን የፕሬስ ድርጅት በድረገጹ አስነብቧል።

በተያዘው በጀት አመት 2016 ከኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት፣ ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭና አገልግሎት 30 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት እየተሠራ እንደሚገኝ አቶ ሞገስ ገልጸዋል ያለው ዘገባው በ2015 በጀት ዓመት ተቋሙ 22 ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ብር ገቢ ከኤክስፖርት፣ ከሀገር ውስጥ ሽያጭና ከአገልግሎት ማግኘቱን በማነጻጸሪያነት ማቅረባቸውንም አካቷል።

በተያያዘ ዜና ኬንያ ከአጎራባቾቿ ሀገራት የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት በሶስት እጥፍ ማደጉን አስታውቃለች። የኬንያ በውሃ ሀይል የምታመነጨው የኤሌክትሪክ መጠን በግድቦቿ የውሃ መጠን ማነስ ምክንያት ከፍተኛ ቅናሽ በማሳያቱ ሳቢያ ከአጎራባቾቿ ሀገራት በመግዛት ለማካካስ መጣሯን ቢዝነስ ደይሊ አፍሪካ ድረገጽ ዘግቧል።

በ2022 ነሃሴ ወር ላይ ከአጎራባቾቿ ሀገራት የገዛችው የኤሌክትሪክ መጠን 208 ነጥብ 47 ሚሊየን ኪሎዋት አዎር ሲሆን በተያዘው 2023 ነሃሴ ወር ላይ ግን መጠኑ 185 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን እና የገዛችው የኤሌክትሪክ መጠን በአሃዝ 594 ነጥብ 01 ሚሊየን ኪሎዋት አዎር መሆኑን አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኬንያ ከአጎራባቾቼ ሀገራት ገዛሁት ካለችው የኤሌክትሪክ ሀይል 70 በመቶ የሚሆነውን የገዛችው ከኢትዮጵያ መሆኑን ድረገጹ ከኬንያ መንግስት ያገኘውን ዳታ መሰረት አድርጎ አስነብቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button