ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ መሪ ዳጋሎ አቀበበልን ተከትሎ ሱዳን በኬንያ ያሉትን አምባሳደሯነ ጠራች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26/2016 .ም፡ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፈጥኖ ደራሹ መሪ መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በናይሮቢ የተደረገላቸውን አቀበበል ተከትሎ በኬንያ የሚገኙ አምባሳደሩን ከማል ጁባራ ለምክክር መጥራቱን አስታወቀ።

የፈጥኖ ደራሹ ጦር መሪ  መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በኬንያ መንግስት ይፋዊ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ይህም ሱዳንን አስቆጥቷል።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ የኬንያ መንግስት በፈጥኖ ደራሹ ሀይል የተፈጸሙ ዘግናኝ የሰብዓው መብት ጥሰቶችን፣ በሀገሪቱ መሰረተ ልማቶች እና አቅም ላይ እንዲሁም በዜጎች ንብረት ላይ ያደረሰውን ጉዳት ዘንግቷል ሲል ኮንኗል።

የሱዳን መንግስት ከአምባሳደሩ ጋር በሚያደርገው ምክክር በሀገራቱ ወደፊት በሚኖረው ግንኙነት ዙሪያ ሁሉንም አማራጮች እንደሚያጤን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አልሳዲቅ መናገራቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ መሪ በኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ፣ ኡጋንዳ እና ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ከሀገራቱ መሪዎች ጋር መክረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button