ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ ድርቅና የበረሃ አንበጣ አማራ ክልልን ጨምሮ በአራት ክልሎች የምግብ ዋስትና ስጋት ደቅኗል- ተመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/ 2016 ዓ.ም፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው አዲስ ሪፖርት በአማራ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በትግራይ ክልሎች በድርቅና ተያያዥ ችግሮች የተስፋፋው የበረሃ አንበጣ የምግብ ዋስትና እጦት አደጋን አባብሷል ሲል ገለፀ።

በአራቱም ክልሎች የተከሰተው ድርቅ እና ተያያዥ ችግሮች የሰብል ምርት፣ የእንስሳት ጤና እና የውሃ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ሲሆን በአፋርና አማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መከሰቱን ድርጅቱ በሪፖርቱ አመልክቷል።

በሰሜን ጎንደር፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ስና ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ዋግ ኽምራ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳድር የተከሰተው ድርቅ ቀድሞውን በምግብ እርዳት ላይ ጥገኛ የነበሩትን በሺዎች የሚጠሩ ተፈናቃዮችን ለከፋ ችግር ዳርጓል ሲል ቢሮው አስታውቋል፡፡ አክሎም በክልሉ ከፍተኛና አሳሳቢ የተመጣጣነ ምግብ አጥረት አጋጥሞታል ብሏል፡፡

በአፋር ክልል ከሐምሌ ወር መጨረሻ ሳምንት ጀምሮ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከተጠቁት አጠቃላይ 13,899 ሰዎች ውስጥ 28 ሰዎች ሞተዋል ያለው ሪፖርቱ የእርዳታ ድርጅቶች በክልሉ የተከሰተው ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳይባባስ አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ብሏል።  

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ በአፋር፣ ድሬደዋ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊ እና ትግራይ ክልሎች 25145 ሄክታር መሬት ላይ የበረሃ አንበጣ በመስፋፋቱ በአካባቢዎቹ የምግብ ዋስትና ላይ ስጋት መደቀኑን አስታውቋል፡፡

በአንዳንድ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ባለው የፀጥታ ችግር የተነሳ ሰፊ ትኩረት ያልተሰጠው የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎቶች እና ተደራሽነት ውስንነት ምክንያት፣ እንደ ኮሌራ፣ ወባና ኩፍኝ ባሉ የበሽታ ወረርሽኝ መከሰቱ የተፈናቀሉ እና ከስደት ተመላሾችን ጨምሮ የተጠቁ ማህበረሰቦችን ለበሽታው ተጋላጭነት የበለጠ እንዲጨምር ያደርጋል” ሲል ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በትግራይ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሪ ሰዎች መፈናቀላቸውን የገለፀው ሪፖርቱ ወደ ቀያቸው ወይም ወደ አማራጭ ቦታዎች ለመመለስ የድጋፍ እጥረት በመኖሩ በ106 ትምህርት ቤቶች ተፈናቃዮች እየተጠለሉ መሆኑን ገልጧል፡፡ በዚህም የተነሳ ለሶስት ተከታታይ አመታት 163 ሺህ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል ነው የተባለው፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button