ዜናፖለቲካ

ዜና: “የትኛውም የድህረ አትሚስ ዝግጅት በጥንቃቄ እና በጥልቀት መመርመር ይገባዋል” ሲሉ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16/2017 ዓ.ም፡- በሶማሊያ ስለሚካሄደው የትኛውም የድህረ አትሚስ ዝግጅት ከመወሰኑ በፊት አስፈላጊ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እና በጥልቀት መመርመር እንደሚያስፈልግ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ማሳሰባቸው ተገለጸ።

ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ይህንን የገለጹት ከ79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኑውዮርክ ባደረጉት ውይይት መሆኑ ተጠቁሟል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ኦሊቨር ኒዱሁንጊሬሄ እና ከኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በተናጠል ተገናኝተው ውይይት ማካሄዳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ ከኡጋንዳ አቻቸው ጄጄ ኦዶንጎ ጋር ያደረጉት ውይይት በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በሶማሊያ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ያካተተ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመላክቷል፤ ሁለቱ ወገኖች የትኛውም የድህረ አትሚስ ዝግጅት ከመወሰኑ በፊት አስፈላጊ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እና በጥልቀት መመርመር እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸውንም አስታውቋል።

ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ለሶማሊያ ሰላም ማስከበር ወታደር ካዋጡ ሌሎች አገራት ጋር በመሆን ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚደረግ ማንኛውም ችኮላ የተሞላበት ስምምነት ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ እስካሁን የተገኙ ስኬቶችን አደጋ ላይ ይጥላል የሚል የጋራ ስጋት እንዳላቸው መግለጻቸውንም ጠቁሟል።

የናይልን ወንዝ በሚመለከት አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ በቀጣይ ጥቅምት ወር ኡጋንዳ የምታስተናግደውን ሁለተኛውን የናይል ጉባዔ ላይ እንደምትካፈል ያሳወቁ ሲሆን ይህም የትብብር ማዕቀፍ ወደ ተግባራዊ ስራ እንዲገባ ለማድረግ እና የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ለማቋቋም ታሪካዊ መሰረት የሚያስቀምጥ ነው ማለታቸውንም አስታወቋል።

የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱ ወደ ተግባር መቀየሩ የጋራ ሀብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም እና በተፋሰሱ አገራት መካከል ያለውን ትብብር ከፍ ለማድረግ አወንታዊ እድገት መሆኑን አምባሳደር ታዬ ጨምረው መግለጻቸውም ተካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተመሳሳይ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩዋንዳው አቻቸው አምባሳደር ኦሊቨር ኒዱሁንጊሬሄ ጋር በነበራቸው ውይይት ሁለቱ ወገኖች የናይልን ወንዝ የውኃ ሀብት ፍትሃዊ እና እኩል ጠቃሚነት በሆነ መልኩ ለመጠቀም ባላቸው የጋራ ፍላጎት ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ የሚያስችል ሀሳብ መለዋወጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ማፅደቋ የናይል ወንዝ ተፋሰስ አገራት ህዝቦች ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀምን ለማረጋገጥ ያላቸውን ፍላጎት ያሳየ ታሪካዊ ውሳኔ መሆኑን ጠቅሰዋል ብሏል።

ሁለቱም ሚኒስትሮች ለትብብር ማዕቀፉ ስምምነት ትግበራ በጋራ ለመስራትም መስማማታቸውንም አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button