ርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕሰ አንቀፅ፡ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በሳዑዲ አረብያ የሚፈጸመው ሰብአዊነት የጎደለው፣ ያልተገባ በደል እና ግድያ ሊያበቃ ይገባል፤ መንግስት እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተጎጂዎች የደረሰባቸውን በደል እያወቁ ቸል ማለታቸው ተገቢ አይደለም!

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 26/ 2015 ዓ.ም፡- የአለም አቀፉ ሰብዓዊ መቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዎች በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የሳዑዲ አረብያ ድንበር ጠባቂዎች በየመን በኩል ድንበሯን አቋርጠው ሊገቡ በሚሞክሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መግደላቸውን አጋልጧል። ተሟጋቹ ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች በተጨማሪ የሳዑዲ አረብያ ድርጊት በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የምርመራ ዘገባ ተረጋግጧል። በአስደንጋጭ ሁኔታ የተጋለጠው የሳዑዲ አረብያ ድርጊት አሁንም ሀገሪቱ በከፋ ሁኔታ በሰብአዊነት ላይ የምትፈጽመውን አሳፋሪ ድርጊት በተለይም በአሰቃቂ ግድያ፣ ለከፋ አካል ጉድለት መዳረግ፣ በጭካኔ አካል መቆራረጥ ተግባራት በይልጥ ያጋለጠ ነው።

ባለፉት አመታት ምንም እንኳ አሳማኝ ማስረጃዎች ቢቀርቡም ሳዑዲ አረብያ የሚቀርብባትን በሰብአዊነት ላይ የምትፈጽመውን የግፍ ውንጀላዎች ሁሉንም ስትክድ ኖራለች። ሳዑዲ ተደጋጋሚ ከምትክዳቸው ክሶች መካከልም በተደራጀ መልኩ ድንበር ጠባቂዎቿ የሚፈጽሙትን ግድያ፣ ወደ ድንበሯ የሚገቡ ስደተኞችን ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ መያዝና፣ በማጎሪያነት የሚያገለግሉ ካምፖች የሚመስሉ በሀገሯ ውስጥ የሚገኙ አሰቃቂ እስር ቤቶቿ ይገኙበታል።

በቅርቡ በሂዩማን ራይትስ ወች ድርጊቱን በሰው ዘር ላይ ተፈጸመ ወንጀል ሲል በማስረጃ አስደግፎ በሪፖርቱ ያካተታቸው ወንጀሎች በሳዑዲ መንግስት በአደባባይ እንዲካዱ ያስቻላቸው በአለም-አቀፍ መንገድ በቀጥታ ተጠያቂ ያለመረጋቸው ውጤት ነው።

ባሳለፍነው አመት ጥቅምት ወር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሳዑዲ ባለስልጣናት በላከው ደብዳቤ ከጥር 1 እስከ ሚያዚያ 30 በሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች 430 ስደተኞች በስልታዊ መንገድ መገደላቸውን፣ የዘፈቀደ፣ ከህግ ሂደት ውጭ ግድያ መከናወኑን ሪፖርት እንደደረሰው ቢያሳውቅም የሳዑዲ መንግስት አጥብቆ ተቋውሟል፤ በተመሳሳይ መልኩ በቅርቡ የወጣውንም ሪፖርት የሳዑዲ መንግስት አልፈጸምኩም ሲል ክዷል።

በቅርቡ በሂዩማን ራይትስ ወች ድርጊቱን በሰው ዘር ላይ ተፈጸመ ወንጀል ሲል በማስረጃ አስደግፎ በሪፖርቱ ያካተታቸው ወንጀሎች በሳዑዲ መንግስት በአደባባይ እንዲካዱ ያስቻላቸው በአለም-አቀፍ መንገድ በቀጥታ ተጠያቂ ያለመረጋቸው ውጤት ነው። ይህ ተጠያቂነት አለመኖር ሀገራት ያለምንም ፍራቻ ድርጊቱን እንዲፈጽሙ ያበረታታል።

የኢትዮጵያ መንግስት በመቶዎች በሚቆጠሩ በዜጎቹ ላይ የሚደርሰው ግድያን በተመለከተ የሚያሳየው ግድየለሽነት እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ የሚያደርጉት እዚህ ግባ የማይባል ጥረት  እግጅ አስደንጋጭ ነው፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ዙሪያ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ነሃሴ 14 ቀን በሰጠው ምላሽ፣ በዋናነት ያሳሰበው የሚመስለው የድርጅቱ ሪፖርት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘመናትን የተሻገረ የዳበረ ግንኙነትን እንዳያበላሸው ነው፡፡ አለፍ ሲልም ምርመራ እስኪደረግ መላምቶችን ከመሰንዘር ታቀቡ በሚል ምክር የታጀበ ነው። ልክ እንደተቀረው አለም ሁሉ የተለመደውን ባዶ ልፍለፋ በመድገም ድርጊቱን ከሳዑዲ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በመሆን እንመረምረዋለን ብሏል።

ሌላው ቢቀር ጠንካራ መግለጫ በማውጣት ለተጠቂዎች የተሰማውን ሃዘን መግለጽ፣ ድርጊቱን በማውገዝ በየተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአለም አቀፍ አጋር ተቋማት በአፋጣኝ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ መጠየቅ ይጠበቅበት ነበር። 

የኢትዮጵያ መንግስት ለተፈጸሙት ወንጀሎች የሳዑዲ መንግስትን ተጠያቂ ማድረግ ባለመቻሉ ዜጎቹን በተደጋጋሚ ከሚፈጸምባቸው ከእንደዚህ አይነት ድርጊቶች ሊታደጋቸው አልቻለም።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ዜጎቹ መንግስት ሰርተው የሚኖሩባት ሀገር መፍጠር ባለመቻሉ ተስፋ በመቁረጥ ሀገራቸውን ጥለው ለመሰደድ በመገደድ ላይ ይገኛሉ። አሳዛኙ ነገር በሳዑዱ ድንበር እየተገደሉ ያሉት አብዘሃኛዎቹ ወጣቶች የሚሰደዱት ጦርነት ካደቀቃቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ከኦሮምያ፣ አማራ እና ትግራይ የሚወጡ ናቸው።

ሀያላን ሀገራቱን ተጠያቂ በማድረግ ፍትህ ለማምጣት ከመሞከር በፊት የፌደራል መንግስቱ ከሁሉም በፊት እጅግ አስቸጋሪ መንገዶችን በመጠቀም ጭምር ወጣቶችን ለስደት እየዳረጋቸው ያለውን የፖለቲካ ልዩነቶችን እና ወታደራዊ ግጭቶችን ሰላማዊ መንገድ በመጠቀም ለመፍታት መጣር ይገባዋል። እንዲሁም የሀገሪቱነ ውስን ሀብት ጦርነትን ለማካሄድ ከማዋል ይልቅ የዜጎቹን ኑሮ ለማሻሻል ማዋል የመንግስት ዋነኛ ትኩረት ሊሆን ይገባዋል።

የሳዑዲ አረብያ አስቸጋሪ እስር ቤቶችን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለሀገራቸው መሬት ለማብቃት የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ስልጣን በተቆጣጠረ ማግስት ሲያደርጋቸው የነበረው ጥረቶች ከፍተኛ ድጋፍ አስገኝቶለት እንደነበር ይታወቃል።

መንግስት ለገጽታ ግንባታ ሲል ያከናውነው እንደነበር በሚያሳብቅ መልኩ በውጭ ሀገራት የሚገኙ የስጋት ተጋላጭ ዜጎቹ ደህንነት እና ሰላም ይልቅ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው ከሳዑዱ መንግስት ጋር ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን መሆኑን አሳይቷል።

እንዳለመታደል ሁኖ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በሂዩማን ራይት ዎች ሪፖርት ዙሪያ የሰጠው ምላሽ የፌደራል መንግስቱ ከሰጠው ምላሽ ያላነሰ የሚያሳዝን ነው። ይህም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁኔታው የሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን እና እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አመላካች ነው።

የሳዑዲ አረብያ መንግስት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ከሚፈጽመው ኢሰብአዊ ተግባሩ እንዲታቀብ አለማድረጉ እየታወቀም ቢሆን እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አለምአቀፉ ማህበረሰብ ለሁኔታው እየሰጠ ያለው ምላሽ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ከመጠየቅ ያለፈ አይደለም።

የመንግስታቱ ድርጅትን ጨምሮ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሳዑዲ አረብያን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ትርጉም ያለው እርምጃ ባለመውሰዱ በስደተኞች ላይ ነውረኛ የሆኑ ተግባራትን እንድትፈጽም እና ግድያ እንድታከናውን አድርጓታል። ይህም በአለም ላይ የሰው ልጆች መብትን በማስከበር ዙሪያ የሚኖረው አስተዋጽኦ የከፋ እንዲሆን ያደርገዋል።

ስለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ፣ ልዩ እና ጠነካራ አቋም በመውሰድ ተጨማሪ ስደተኞች በሳዑዲ ድንበር እንዳይገደሉ ማድረግ ይኖርበታል። ግድያ የተፈጸመባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ፍትህ እንዲያገኙ ለማስቻል ተጠያቂነትን በማምጣት ሳዑዲ አረብያ ጉዳዩነ በአፋጣኝ እንድትመረምር ማድረግ ይገባል።

የበርካታ ዜጎች ህይወት አደጋ ላይ ነው፤ እስካሁን በዚህ አሰቃቂ ድርጊት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ግን የኢትዮጵያ መንግስት እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ቸልታ አይገባቸውም።አስ

ተጨማሪ አሳይ
Back to top button