ዜናርዕሰ አንቀፅ
በመታየት ላይ ያለ

ርዕስ አንቀጽ: የኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የውስጥ ቀውሶች ከመቸውም ግዜ በላይ ሙሉ ትኩረት ይሻሉ፤ ትኩረት መንፈግ በሀገር ላይ አደጋ መደቀን ነው!

አዲስ አበባ፣ ጥር 24/2016 ዓ.ም፡- ውስብስ እና ዘርፈ ብዙ የሀገር ውስጥ፣ ቀጠናዊ እና አለም አቀፍ ተግዳሮቶች ኢትዮጵያን ከምንግዜም በላይ እየፈተኗት ይገኛሉ። የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ እንዲሁም በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያሉት ግጭቶች በሀገር ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው ሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሯል።

“በጦርነት፣ ግጭቶች እና በተደጋጋሚ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ከሃያ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የምግብ ዋስት ስጋት ያጋጠማቸው ሲሆን፤ 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚሆኑት አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።”

በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በመካሄድ ላይ ባሉ ገዳይ ግጭቶች፣ ድርቅ እና ጎርፍ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ ምንም አይነት የምግብም ሆነ የመድሃኒት ድጋፍ በሌለበት ሁኔታ ኑሯቸውን እየገፉ ነው።

ተመጣጣኝ ያልሆ ጦርነት፣ ግጭት እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጽንፍ የያዘ ማህበረሰብ እንዲፈጠር አድርጓል። ይህም የማህበረሰቡን ውቅር፣ ትስስር እና ብሔራዊ አንድነት  አደጋ ላይ ጥሎታል

አብዘሃኛው የሀገሪ ዜጎች በሚኖሩባቸው ትላልቆቹ የሀገሪቱ ክልሎች ማለትም ኦሮምያ እና አማራ በመካሄድ ላይ ያሉት ግጭቶች የኢኮኖሚውን እንቅስቃሴ ገድበውታል። ግጭቶቹ በተለይም ለህብረተሰቡ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎች እና ማዳበሪያ እንዳይጓጓዝ አደናቅፈዋል፤ የግብርና ምርቶች እንዲያሽቆለቁል አድርገዋል። እነዚህ ችግሮች ላይ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና አሳሳቢ የሆነ የዋጋ ግሽበት ተጨምረውበት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እጅግ ተፈትኗል። ሀገሪቱን ወደ አልታወቀ እና አሳሳቢ መንገድ እየመራት ይገኛል።  

ተመጣጣኝ ያልሆ ጦርነት፣ ግጭት እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጽንፍ የያዘ ማህበረሰብ እንዲፈጠር አድርጓል። ይህም የማህበረሰቡን ውቅር፣ ትስስር እና ብሔራዊ አንድነት አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ኢትዮጵያውያንን በብሔራዊ ጥቅሞቻቸው ዙሪያ እንኳ እንዳይሰባሰቡ እና ከምንግዜውም በላይ እንዲከፋፈሉ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ከቀጠናው ጋር በተያያዘ በቅርቡ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ በአፍሪካ ቀንድ እና በዙሪያው ውጥረት ከማስፈኑ ባለፈ ኢትዮጵያ ከጎረቤቷ ከሶማሊያ ጋር የነበራትን ግንኙነት አሻክሮታል። ከዚህም ባለፈ ሶማሊያ በፕሬዝዳንቷ አማካኝነት ከኢትዮጵያ ጋር የሻከረ ግንኙነት አላቸው ብላ ያሰበቻቸውን እንደ ግብጽ እና ኤርትራ መሰል ሀገራት ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን ለማጥበቅ እሩጫ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተጨማሪም የመግባቢያ ሰነዱ የዲፕሎማሲ ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል፤ የተደረሰውን ስምምነት ቀጥታ ባያወግዙትም በርካታ ሀገራት ለሶማሊያ አጋርነታቸውን በማሳየት ላይ ናቸው፤ የሶማሊያ ሉዐላዊነትና  ግዛታዊ አንድነትን እንዲጠበቅ እንፈልጋለን እያሉ ነው። ይህም ከሁለት አመቱ የትግራይ ጦርነት በኋላ እያገገመ የነበረውን የሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ አላስፈላጊ ጥላ አጥልቶበታል።

የአለም አቀፍ ቅቡል አሰራርን እና መርህን ተከትሎ በአግባቡ ካልተያዘ ወደ አደገኛ አዙሪት እንድንገባ በማድረግ ከአለም አቀፍ እና የአህጉሩ ሃያላን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት እና የመሰረተችውን አጋርነት አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል።  

በበርካታ የውስጥ ችግሮቿ እየተናጠች ያለች ሀገር በምንም መልኩ ብሔራዊ ጥቅሟን ልታስከብር አትችልም፤ ተለዋዋጭ በሆነው እና በቀውስ በሚታመሰው ቀጠናም ሉዓላዊነቷን ማስከበር አዳጋች ሊያደርገው ይችላል

መንግስት ከሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ የፈረመው በውስጥ ችግሮቿ እየተናጠቸ ያለችውን ሀገር የውስጥ አጀንዳዎቿን በማስቀየስ አንድ የሚያደርጋት ሀገራዊ ጀንዳ ለመፍጠር በሚል ነው ሲሉ ብዙዎች እንደመከራከሪያ በማንሳት ላይ ይገኛሉ። የባህር በር በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅቡል አጀንዳ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ለዚህም ይሆን አይሆን የባህር በር ማግኘት የሚለው ጉዳይ ዋነኛ ብሔራዊ አጀንዳ ሁኗል፤ የሀገር ውስጥ ወሳኝ እና ተቀጣጣይ ጉዳይ ሁኗል።

የሚያሳዝነው ነገር በተመሳሳይ መልኩ ጉዳዩ ኢትዮጵያውያንን የከፋፈለ አጀንዳም መሆኑ ነው፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያውያንን በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ጎራ ከፍሏቸዋል። ልዩነትን ማቻቻል እና ያለፈ ቁስል ማከም የሚሉ ዋነኛ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገባበት በዚህ አንገብጋቢ ወቅት ይሄ መፈጠሩ የሚያጸጽት ነው። የባህር በር የሚል አጀንዳን በማስቀደም እነዚህ አንገብጋቢ ሀገራዊ ጉዳዮችን ችላ ማለት የፖሊሲ አቅጣጫንም ሊያቀይስ ሆነ፣ የኢትዮጵያን ሉዐላዊ የባህር በር የማግኘት ፍላጎትንም ሊያስት አይችልም።

በበርካታ የውስጥ ችገሮቿ እየታመሰች ያለች ሀገር ብሔራዊ ጥቅሞቿን ማስጠበቅም ሆነ መቀየስ አትችልም። ተለዋዋጭ በሆነው እና በቀውስ በሚታመሰው ቀጠናም ሉዓላዊነቷን ማስከበር አዳጋች ይሆንባታል። በታህሳስ ወር ርዕሰ አንቀጻችን እንዳቀረብነው የመከራከሪያ ሀሳብ በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያሉ ግጭቶችን በድርድር በአፋጣኘ ማስቆም የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ነው።

ሚሊዮኖችን ወደ ችግር አፋፍ አየገፋቸው የሚገኘው በሀገሪቱ የተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ እና አሳሳቢው የኢኮኖሚ ሁኔታም በእኩል ደረጃ የመንግስትን ሙሉ ትኩረት ይሻል። የተሳሰረ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንዲቻል የተንሰራፉ ሀገራዊ ከፋፋይ ትርክቶችን መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ዋነኛ ትኩረት ሊሆን ይገባዋል። በተመሳሳይ፣ ትኩረት መንፈግ ማለት የሀገሪቱን ሉዐላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ መጣል ማለት ነው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button