ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በሱዳን ጉዳይ የሚመክር ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ነገ ይጀመራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9/2016 ዓ.ም፡- በሱዳን ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሔ ለመፈለግ ያለመ የሱዳን ሲቪል ተቋማት ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚቆይ በአዲስ አበባ ኮንፈረንስ እንደሚያካሂዱ ተገለጸ።

የሱዳን ሲቪል ሀይሎች በአዲስ አበባ በሚያካሂዱት ኮንፈረንስ ዋነኛ ትኩረት የሚሆነው በሀገሪቱ የተከሰተውን ግጭት እልባት ለማስገኘት የሚያስችል ስትራቴጂ መቀየስ መሆኑን ራድዮታማዙጂ በድረገጹ ባቀረበው ዘገባ አመላክቷል።

በሳምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ የሚደረገውን ኮንፈረንስ ለማሳለጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የሱዳን ብሔራዊ ፓርቲ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው ኡማ ፓርቲ የሚዲያ ሃላፊ ሚስባህ አህመድ መሃመድ አረጋግጠዋል።

ኮንፈረንሱ ከ70 በላይ የሚሆኑ ከተለያዩ የሱዳን ሲቪል ተቋማት እና ተጽእኖ ፈጣሪዎችን ተሳታፊ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።  

የኮንፈረንሱ ዋነኛ ግብ በቀጣይ ወር መጀመሪያ ለሚካሄደው ሁሉን አቀፍ አጠቃላይ ኮንፈረንስ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እና ዝግጅቶችን ማድረግ መሆኑን የኡማ ብሔራዊ ፓርቲ የሚዲያ ሃላፊው ሚስባህ አህመድ መሃመድ ገልጸዋል። በኮንፈረንሱ የሀገሪቱን የእርስ በርስ ግጭት በማስቆም የጋራ የፖለቲካ ራዕይ እንዲኖር የሚያስችል ዝግጅት በማድረግ የዲሞክራሲ ሁደቱን ማስጀመር መሆኑንም አመላክተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button