ዜናህግ እና ፍትህ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን እና ምዕመናንን መግደላቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18/ 2016 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ እና ምሥራቅ አርሲ ዞኖች ታጣቂዎች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት እና ምዕመናን ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ሰኞ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም. ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።  

ቢቢሲ አማርኛ ጥቃቱን በተመለከተ በሰራው ዘገባ፤ ሁለቱ አገልጋዮች ከነ ቤተሰቦቻቸው ከመገደላቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ እሁድ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም. አንድ የ80 ዓመት ሴት አዛውንት እና ሌላ ወጣት ምሥራቅ አርሲ ውስጥ በአስቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ዘግቧል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንድ የሃይማኖት አባት፤ ታጣቂዎች ወጣቷን እናት ከገደሉ በኋላ ባለቤቷን እና ልጇን አግተው መውሰዳቸውን ገልጸዋል። አክለውም ከሁለቱ እናቶች ግድያ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በሚገኘው ማሊንጮ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ላይ ዘረፋ መፈጸሙን ገልጸዋል።

በምሥራቅ አርሲ ዞን የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ የሆኑት ቄስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቤተክርስቲያንን እና ምዕመናንን ዒላማ ባደረጉ ጥቃቶች ከመስከረም 2016 ዓ.ም. ወዲህ በአካባቢው ከ80 ያላሱ ሰዎች ተገድለዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት መጋቢት 8/2016 ዓ.ም. ደግሞ አንድ ቄስ ከእነ ባለቤታቸው በዚሁ ዞን ሽፎ በሚባል አካባቢ መገደላቸውን የቤተክርስቲያኗ ምንጭ ገልጸዋል።

“እነዚህ ጥቃቶች ቤተክርስቲያን እና ክርስቲያኖች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው” በማለት ገልጸዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአካባቢው በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ፈጻሚው ማን እንደሆነ በግለጽ እንደማያውቁ የሚናገሩት ቀሳውስት እና ምዕመናን፣ የመንግሥት አካላት ግን አማጺውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን በተጠያቂነት ይከሳሉ።

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞኖች ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰል ጥቃት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዞኑ ሽርካ ወረዳ፤ ህዳር 13 እና 17 ቀን ማንነታቸው ባልተለየ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ከ36 በላይ የኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች መገደላቸውን ኢዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወሳል።  ነዋሪው በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ህጻናት እና አዛውንቶች እንደሚገኙበት ገልጸዋል። 

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በወቅቱ፣ ጥቃቱን የፈጸመው፣ መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ የሚጠራው ዐማፂ ኃይል መሆኑን ገለጸው በጥቃቱም 27 ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button