ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ምዕራብ ትግራይ በአማራ ሀይሎች ቁጥጥር ስር በመሆኑ አሁንም የትግራይ ተወላጆች የሚደርሰው መፈናቀል እና ግፍ ቀጥሏል

በምህረት ገ/ክርስቶስ @MercyG_kirstos

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 26/2015 ዓ.ም፡- በአማራ ሀይሎች ቁጥጥር ስር በሚገኘው የምዕራብ ትግራይ አሁንም በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው መፈናቀል እና ግፍ ቀጥሏል። በአምስት ቀናት ብቻ 1436 ተፈናቃዮች በሽሬ አቅራቢ በሚገኘው እንዳባጉና መጠለያ ካምፕ መድረሳቸው ተጠቁሟል። መጠለያ ካምፑ ከአስራ አንድ የአከባቢው ወረዳዎች ማለትም ቃፍታ፣ ሁመራ፣ ቆራሪት፣ ወልቃይት፣ ሰቲት፣ ማይካድራ እና ዳንሻ የሚፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።

በቅርቡ የፕሪቶርያው ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ቀያቸውን ጥለው በመሰደድ ላይ የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ስደተኞች ለስደታቸው ዋነኛ ምክንያቶች በአከባቢው የሚካሄደው ጅምላ እስርን ለመሸሽ እና በረሃብ ሳቢያ መሆኑን በመጠለያ ካምፑ የስደተኞች አስተባባሪ የሆነው ሙሉጌታ ደባልቀው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

የመጠለያው አስተባባሪ በተጨማሪም በማይጸብሪ፣ ዲማ እና ጸለምት በርካቶች ለእስር ተዳርገው ከፍተኛ ግፍ ሲፈጸምባቸው የነበሩ በመጠለያው ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቀው አንዳንዶቹ 135ሺ ብር ማስለቀቂያ እንዲከፍሉ መገደዳቸውን ጠቁመዋል። እንደ ሙሉጌታ ደባልቀው ገለጻ በአከባቢው በሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎች ላይ የሚደርሰው ግፍ እና እስራት የተበራከተው በአከባቢ የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎችን የሀገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት ትጥቅ ማስፈታት ይጀምራል የሚል መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ነው።

በወልቃይት ለሰባት ወራት በእስር ካሳለፉ በኋላ በመከላከያ ወታደሮች ከመገደል የተረፉ ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እነዲገለጽ ያልፈለጉ ሽማግሌ አባት ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት በእስር በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ይደርስባቸው እንደነበር እና ምግብም ይከለከሉ እንደነበር ገልጸው ከእስር ቤቱ በማውጣት በዛሪማ ግድብ አከባቢ ሊገድሏቸው እየተወሰዱ እያለ መከላከያ ወታደሮች በመድረሳቸው ሂወታቸውን እንዳተረፏቸው እና ወደ እንዳባጉና መጠለያ እንዳደረሷቸው አስታውቀዋል።

የመጠለያው አስተባባሪ ሙሉጌታ በመጠለያው የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች እርዳታ ከተሰጣቸው አመት አልፏቸዋል፤ በመጠለያው ያለው ሁኔታ እጅግ የከፋ መሆኑን አስታውቀዋል።  

ከቤተሰብ በሚሰጣቸው ድጋፍ፣ የቀን ስራ በመስራት እና በልመና ሂወታቸውን በመግፋት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለመጠለያ ካምፑ የሚሰጡት ትኩረት እጅግ አናሳ መሆኑን ገልጸዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button