ፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የሳዑዲ አረብያ መንግስት ድንበር ጠባቂዎቹ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙትን ግድያ አስመልክቶ የሂዩማን ራይት ዎች ያወጣውን ሪፖርት አጣጣለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 16/2015 ዓ.ም፡- ሳዑዲ አረብያ ድንበር ጠባቂዎች በየመን በኩል ድንበሯን አቋርጠው ሊገቡ የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መግደላቸውንና ድርጊቱ በሰብአዊነት ላይ ተፈጸመ ወንጀል ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣው ሪፖርት የሳዑዲ አረብያ መንግስት መሰረተ ቢስ፣ ከታማኝ ምንጮች ያልተገኘ ሲል አጣጣለ፡፡

በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ አረበያ ሊገቡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከየካቲት ወር 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ድረስ በሳኡዲ አረብያ ድንበር ጠባቂዎች በኩል በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸውን  አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋሙ ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታውቋል፡፡

የሳኢዲ አረብያ መንግስት ከተቀረው አለም በተደበቀ መልኩ በርካታ ሴቶች እና ህጻናትን እየገደለ ነው ሲል ተችቷል። የሳኡዲ አረብያ መንግስት ስደተኞችን እና ጥገኝነትን በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ገዳይ መሳሪያ መጠቀም የሚፈቅድ ማንኛውንም ፖሊሲዎቿን እንድታስወግድ ተቋሙ ጠይቋል።

ይህንን ተከትሎ የሳዑዲ ባለስልጣናት ድንበር ጠባቂዎቹ በኢትዮጵያውያን ላይ ፈፅመዋል የተባለውን  ግድያ   ማስተባበላቸውን አልጀቸዚራ ባሰራጨው ዘገባ አስታውቋል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርቱ ጉዳዩ የሚያሳስባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን ጫና እንዲፈጥሩ የጠየቀው ሂዩማን ራይት ዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን እንዲያጣራ ጥሪም አቅርቦ የነበር ሲሆን፣  የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩ እጅጉን አሳስቦኛል፣ የሳዑዲ መንግስት ሁኔታው በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ መፍቀድ ይኖርበታል ስትል በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል አቋሟን አስታውቃለች፡፡ ሁኔታውን አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት ከሳዑዲ መንግስት ጋር መነጋገሯንም አስታውቃለች።

የአሜሪካ መንግስት ለሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ምንም አይነት እገዛም ይሁን ስልጠና ሰጥቶ እንደማያውቅ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በኩል መናገሩን ዘ ኒው አረብ ድረገጽ አስነብቧል።

ሂዩማን ራይት ዎች ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳስታወቀው የሳኡዲ አረብያ ድንበር ጠባቂዎች በየመን በኩል ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ የሚፈጥሩ መሳሪያዎችን እንደሚጠቀሙ እና በቅርብ እርቀት ላይም የሚገኙትንም ተኩሰው እንደሚገድሉ አመላክቷል።  አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button