ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ሶስት የንግድ መርከቦች በቀይ ባህር አቅራቢያ በየመን ሁቲ አማጽያን የሚሳኤል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24/2016 ዓ.ም፡- የየመን ሁቲ አማጽያን በቀይ ባህር በሶስት የንግድ መርከቦች ላይ የባለስቲክ ሚሳኤል መተኮሳቸው ተገለጸ።

በተመሳሳይ አማጽያኑ ሃላፊነት የወሰዱበት የድሮን ጥቃት በአሜሪካ የጦር መርከብ የፈጸሙ ሲሆን የአሜሪካ የጦር መርከብ ሶስቱ ድሮኖች መትቶ መጣሉን አሶሼትድ ፕሬስ የዜና አውታር በዘገባው አስታውቋል።  

የእስራኤል ሃማስ ጦርነትን ተከትሎ አማጽያኑ በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመሩ ተጠቁሟል።

ጥቃቶቹን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቋል ያለው ዘገባው  በአለም አቀፍ የባህር ንግድ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው ሲል የሁኔታውን አሳሳቢነት መግለጹን አመላክቷል። በቀይ ባህር ላይ በመፈጸም ላይ ያሉት ጥቃቶች በሁቲ አማጽያን ይፈጸሙ እንጂ ጥቃቶቹን በማስቻሉ ረገድ ዋነኛ ተዋናይ ኢራን ነች ሲል ወንጅሏል።

በኢራን እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው አማጽያኑ በትላንትናው እለት ጥቃት ከሰነዘሩባቸው መርከቦች መካከል የባሃማስ እና የፓናማ ባንዲራን ሲያውለበልቡ በነበሩ መርከቦች ላይ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button