ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና በመስጠት የባህር በር ለማግኘት መስማማቷ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23/2016 .ም፡ ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባህር በር ለመስጠት እና በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

ትላንት ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ጠ/ሚኒስትር አቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰንድ ተፈራርመዋል።

እንደ ሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጫ ከሆነ የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባህር በር ለመስጠት እና በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት የሚያስችል ነው።

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለአዲስ ስታንዳርድ የላከው መገለጫ እንደሚያመላክተው የተፈረመው ታሪካዊ ስምምነት ኢትዮጵያ ለባህር ሀይሏ የሚሆን ቦታ ከሶማሊላንድ የሚያስገኝላት ሲሆን በተመሳሳይ ማንም ሀገር እውቅና ሰጥቷት የማታውቀው ሶማሊላንድ ደግሞ ከኢትዮጵያ ሙሉ እውቅና እንድታገኝ ያደርጋታል ብሏል።

በኢትዮጵያ በኩል ጉዳዩን አስመልክቶ የወጣው መግለጫ እንደሚያመላክተው የመግባቢያ ሰነዱ መፈረም የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት እውን የሚያደርግ፣ የባህር በር አማራጮችን የሚያሰፋ፣ የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር ነው ብሏል።

የሶማሊላንድ መንግስት መግለጫ እንደሚያሳየው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ከስምምነቱ ፊርማ በኋላ ባደረጉት ንግግር የአንድ ሀገር ፕሬዝዳንት በሀላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ለህዝቡ ዪጠቅመውን ነገር ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ለባህር ሀይላቸው የወደብ አቅርቦት ፍላጎት ለማሟላት ለጎረቤት ሀገራት ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታውቀው ሀገራቸው ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ እውቅና ለማግኘት በርካታ አመታትን በትእግስት መጠበቋን ገልጸዋል።

ሶማሊላንድ ለቀጣይ 50 አመታት ለኢትዮጵያ የባህር ሀይል መቀመጫነት የሚያገለግል 20 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው የባህር ላይ መሬት በመስጠት በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ሙሉ እውቅና እንድትሰጥ የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ላይ መድረሳችንን ስገልጽ በደስታ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ተናግረዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button