ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል ግማሽ በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች አሁንም በጸጥታ ችግር ወደ ትምህርት ገበታ አለመመለሳቸውን የክልሉ መንግስት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል በተያዘው የትምህርት አመት በጸጥታ ችግር ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱ ተማሪዎች 50 በመቶ የሚጠጉት መሆናቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ መናገራቸውን አሚኮ በዘገባው አመላክቷል።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት እክል ከገጠማቸው ተቋማት ውስጥ የትምህርት ሴክተሩ አንዱ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው በክልሉ ምሥራቅ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አሁንም ድረስ ትምህር አለመጀመሩን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊዋ መናገራቸውን አስታውቋል።

በእነዚህ ዞኖች ውጭ በሚገኙ የክልሉ አካባቢዎች 60 በመቶ የአንደኛ ደረጃ እና 55 በመቶ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ብቻ በመማር ላይ እንደሚገኙ ያመላከተው ዘገባው ለዚህ ደግሞ የጸጥታው ችግር አሁንም ሥጋት መኾኑን በምክንያትነት ሃላፊዋ ማስቀመጣቸውን አካቷል።

በክልሉ በየጊዜው ሰላም በሚኾንባቸው አካባቢዎች ከጸጥታ መዋቅሩ እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ አየተሠራ እንደሚገኝ ሃላፊዋ ዶ/ር ሙሉነሽ መናገራቸውን አስታውቋል።

የትምህርት ግብዓት የማሟላት እና የመማር ማስተማር ሂደቱን የማስጀመር ሥራም እየተሠራ ነው ሲሉ ሃላፊዋ ተናግረዋል ያለው ዘገባው በተያዘው የትምህርት ዘመን የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ እንዲቻል ቢሮው የዓመቱን የትምህርት ሥርዓት እንደገና ለማሻሻል ጥናት እያደረገ እንደሚገኝም መግለጻቸውንም አካቷል።  

በተለይም ደግሞ በዚህ ዓመት የክልል እና ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የባከኑ ጊዜያትን በልዩ ሁኔታ ለመሸፈን ከመምህራን እና ርዕሰ መምህራን ጋር ውይይት እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል ብሏል።

በተፈናቀሉ እና በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎችም መንግሥት ከሚሠራው ሥራ ባለፈ ረጅ ድርጅቶች፣ የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ እየተሠራ መኾኑንም ጠቁሟል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውንም ዘገባው አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button