ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ከድርቅ ጋር በተያያዘ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ከ5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተጎጂዎች መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21/2016 ዓ.ም፡- ከድርቅ ጋር በተያያዘ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ከአምስት ሚሊየን በላይ ሰዎች ተጎጂ መሆናቸውነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኦቻ አስታወቀ።

በአማራ ከሶስት ነጥብ አምስት ሚሊየን የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች በእርሻ ሰብላቸው መጎዳት እና በተባይ መሰራጨት እንዲሁም በክልሉ በመካሄድ ላይ ባለው የትጥቅ ግጭት ሳቢያ ለተረጅነት የተጋለጡ መሆናቸውን ጠቁሟል።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል ከሁለት ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች በምግብ እጥረት ችግር እንደሚያጋጥማቸው ያመላከተው የመንግስታቱ ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮው በምክንያትነት ያስቀመጠውም የክልሉ የመኸር እርሻ ምርት መጠን ከአማካኝ በታች እንደሚሆን የተደረገው ዳሰሳ በማሳየቱ መሆኑን አስታውቋል።

በአማራ ክልል በተለይም በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን እና ደቡብ ሸዋ እና በኦሮምያ ልዩ ዞን ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ሊኖሩ የሚችሉ ተረጂዎችን ለመለየት እና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች የዳሰሳ ጥናት መደረጉን ማስተባበሪያው አስታውቋል። የፌደራል መንግስት 170ሺ ለሚሆኑ በሰሜን ወሎ ለሚገኙ እና 35ሺ ለሚሆኑ በደቡብ ወሎ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ማደሉን አመላክቷል። የፌደራል መንግስቱ የምግብ እርዳታ እጥረት በሚያጋጥበት ወቅት ለመሸፈን ጥረት እያደረገ መሆኑን የጠቆመው የመንግስታቱ ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮው በትግራይ ክልል በ24 ወረዳዎች ለሚገኙ 361ሺ ተጎጂ ተፈናቃዮች የምግብ እርዳታ ማቅረቡን አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button