ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ለመሳተፍ እና የድርሻዋን እንድትወጣ እድሉ እንዲያመቻችላት ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20/2016 .ም፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ሲያካሄድ የነበረውን አመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቋል።

መደበኛ ስብሰባውን ካጠናቀቀ በኋላ ሲኖዶሱ በሰጠው መግለጫ ቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎና ሚና በተመለከተ በስፋት መወያየቷን ጠቁሞ ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ ችግሮችን እንደሚፈታና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚነገሩትን የሐሰት ትርክቶች ሁሉ የሚታረሙበት እንደሚሆን ያላትን እምነት ገልጻለች።

በመሆኑም ቤተክርስቲያኗ በምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎና ሚና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና እንዲፈጸም መወሰኗን ያመላከተው የሲኖዶሱ መግለጫ የምክክር ኮሚሽኑም ይህን የቤተ ክርስቲያኗን እቅድ በመርሐግብሩ በማካተት ቤተ ክርስቲያኗ የድርሻዋን እንድትወጣ እድሉን እንዲያመቻችላት በጉባኤው በኩል ጥሪ ማቅረቧን አስታውቋል፡፡

ሲኖዶሱ በመግለጫው ካነሳቸው ሀሳቦች መካከል በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገሪቱ ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት የሀገሪቱ ህዝቦች ገና ሳይጽናኑ በሌሎች የሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን በእጅጉ አሳዝኖታል የሚለው ይገኝበታል።

በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላቸው በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የበኩላችሁን ሚና በመወጣት የሀገሪቱነ ሰላምና አንድነቷን እንዲያስጠብቁ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

ስለ ሀገሪቱ ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያኗ አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጽሙ ትዕዛዝ አስተላልፏል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button