ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የአማራ ክልል የአምስት ወራት ስራ አፈጻጸሙን ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12/2016 .ም፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የአምስት ወራት ስራ አፈጻጸሙን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡ ተገለጸ።

በአማራ ክልል የተከናወኑ “የህግ-ማስከበርና የአመራር መልሶ ማደራጀት” ስራዎች ክልሉ ወደ ተጨባጭ “የልማት እንቅስቃሴዎች” እንዲገባ አስችሏል ተብሏል።

በክልሉ “ሰላም እየሰፈነ” በመሆኑ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ጨምሮ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና “የልማት ስራዎች በተሟላ ሁኔታ” መከናወን ጀምረዋል ብሏል።

የመከላከያ ሰራዊትና ህዝቡ በመቀናጀት በሰሩት ስራ ክልሉ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሷል ሲሉ በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ አስተባባሪ እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል ያለው የኢዜአ ዘገባ አሁን ላይ “የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት” በእጅጉ መሻሻሉን በመጠቆም “በክልሉ ተደቅኖ የነበረው አደጋም ሙሉ በሙሉ ተቀልብሷል” ማለታቸውን አስታውቋል።

የክልሉን “የጸጥታ መዋቅር እንደገና በማደራጀት ወደተሟላ ተልእኮ ማስገባት” ተችሏል ማለታቸውን አካቷል።

በሁሉም “የክልሉ አካባቢዎች ወደ ልማት ስራ” ተገብቷል ማለታቸውንም አስታውቋል።

በክልሉ ባለፉት አምስት ወራት እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ አመራር የማደራጀት ስራዎች ተከናውኗል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ ተናግረዋል ያለው ዘገባው የጸጥታ መዋቅሩም እንደገና መደራጀቱን በመግለጽ “ባለፉት አምስት ወራት በሶስት ዙሮች ከ20 ሚሊዮን በላይ የክልሉ ህዝብ ጋር ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል” ማለታቸውን አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ በበኩላቸው በአማራ ክልል “በተደረገ የህግ ማስከበር ተግባር ቡድኑ መዳከሙን ገልጸዋል” ሲሉ ገልጸዋል ያለው ዘገባው የክልሉ ህዝብ ህግ ማስከበር ዘመቻውን ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን እየደገፈ መሆኑን በመጥቀስ “በተሳሳተ ቅስቀሳ ወደ ጽንፈኛ ቡድኑ የተቀላቀሉ ወጣቶችም በመመለስ” ላይ ይገኛሉ ማለታቸውን አካቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ “ከመጠናቀቁ በፊት ባሉት ጊዜያት” ውስጥ የሚሰሩ ተግባራትን አጠናቆ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ማስቀመጡን ዘገባው አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button