ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የአንድ ወገን ብቻ አድርጎ ማየት ሀገርን እንደመካድ ይቆጠራል ሲል የአማራ ክልል መንግስት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27/2016 ዓ.ም፡- የአማራ ክልል መንግስት የሁሉም በሁሉም የሆ ነው ያለውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወገን ብቻ አድርጎ ማየት ሀገርን እንደመካድ ይቆጠራል ሲል ገለጸ።

የክልሉ መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መልዕክት መከላከያ ሀይሉ ጠላት እንደሚናገረው ከአንድ ወገን ብቻ የተዋቀረ ወይም የአንድ ብሔር ስብስብ አሊያም የአንድ የፖለቲካ ፓርቲን ጥቅም አስጠባቂ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ከሚገኙ ሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተውጣጣ ከአንዲት ኢትዮጵያ ማህፀን ተፀንሶ ለሀገር ሰላምና ሉአላዊነት ክብር የተወለደ ነው ሲል ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የተዋጣለት የመከላከያ ሀይል አላት ሲል ያወደሰው የክልሉ መንግስት መግለጫ ሆኖም በዚህ ወቅት ባልተለመደ መልኩ መከላከያ ሰራዊቱን አቅም እንደሌለው፤ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ጠባቂና ተልእኮ ፈፃሚ እና ከአንድ ወገን ወይም ብሔር ብቻ የወጣ አድርጎ የመመልከት እሳቤ በግልም ሆነ በህቡዕ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እየተንጸባረቀና እየተነገረ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው ሲል ገልጾ ይህ ለሰራዊታችን የተሰጠ የዳቦ ስም መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል።

የመከላከያ ሰራዊቱን ከሚጠብቀው ከአብራኩ ከወጣበት ህዝብ ለመነጠል የሚደረገው ግብግብ በምንም መለኪያ ተቀባይነት አይኖረውም ሲል ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button