ዜናጤና

ዜና፡ የጤና ቀውስ በተባባሰበት ኦሮሚያ በገጠር ተመድበው የማገልገል ፍላጎት ያላቸው ሃኪሞች በለመግኘታቸው የሚፈለገውን ያህል ዶክተሮች መቅጠር አለመቻሉን ቢሮው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10/ 2016 ዓ/ም፦ የጤና ቀውስ እየተባባሰ ባለበት ኦሮሚያ ክልል፣ በ2016፣ 1100 ሃኪሞችን ለመቅጠር የክልሉ ጤና ቢሮ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ቢያወም በገጠር ተመድበው የማገልገል ፍላጎት ያላቸው ሃኪሞች ቁጥር አናስ በመሆኑ የተመዝገቡት ሃኪሞቸ በዛት ከ300 በታች መሆኑን ቢሮው ለአዲስ ሰታንዳርድ አስታወቀ፡፡ 

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ደረጀ አብዳና የቅጥር ማስታወቂያ  ሰኔ  2015 ወጥቶ ለሁለት ወር ያህል ቢቆይም የሚፈለገውን ያህል ተቀጣሪ ማግኘት እንዳልተቻል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

“የተቀጠረው ሰው 300 አይሞላም። ይህ ለዘንድሮ በጀት ከተመደበው የሰራተኞች ብዛት ጋር ሲነፃፀር በጣም ያነሰ ነው። ለአሁኑ ክፍተቱን ለመሙላት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን እና ነርሶችን ቀጥረናል። የተፈለገውን ያህል ሰራተኛ ያጣነው የተማረ የሰው ሃይል ታጥቶ ነው ብለን አናምንም፣ ሌላ ምክንያት ይኖራል ብለን እናስባለን” በለዋል፡፡

ሃላፊወ ሌላ ምክንያት ሲሉ ያበራሩት፣ ገጠር ላይ ተቀጥሮ የመስራት ፍላጎት አለመኖር መሆኑን ነው፡፡ “ በዙ ሰው እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ላይ ነው መቀጠር የሚፈልገው። እኛ ደግሞ የጤና ባልሙያ እጥረት ያለብን በገጠር ነው እንጂ በከተሞች ላይ እይደለም” በለዋል፡፡

አቶ ደረጄ እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ በመላ ኦሮሚያ ክልል የድጋፍ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ወደ 90,000 የሚጠጉ የጤና ባለሙያዎች ያሉ ሲሆን ነገር ግን ይህ ቁጥር ክልሉ ስፋት እና ከክልሉ የጤና አጠባበቅ አገልግሎት እጥረት አንጻር ሲታይ በጣም ዝቅተኛ ነው።

በተለይም እንደ ወባና ኮሌራ ያሉ በሽታዎች እየተባባሱ ባለባቸው በርካታ የክልሉ ወረዳዎች የሐኪሞች እጥረት ተፈጥሯል ብለዋል። ይህንን ለመፍታትም የባለሙያ ጥቅር ሊደረግ ይገባል ያሉት ኃላፊው ቢሮው አሁንም በድጋሚ የቅጥር ማስታወቂያ ለማውጣት ማቀዱን ተናግረዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button