ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ምክር ቤቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን ጨመሮ አራት ረቂቅ አዋጆችን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4/ 2016 ዓ/ም፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት መካከል የተደረገውን በሁለትዮሽ ወታደራዊ ቴክኒካዊ ትብብር ወቅት የተገኙ የፈጠራ ሥራ ውጤቶች እና ንብረቶች የጋራ ጥበቃ ስምምነት አዋጆችን አጸደቀ። 

ምክር ቤቱ አዋጁን ያጸደቀው በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባዔ ነው።

በጉባዔው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ  በሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን፤ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየት አቅርበዋል።

ለቀረበው ጥያቄና አስተያየት በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፤ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1310/2016 ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል ተብሏል።

መክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት መካከል የተደረገውን በሁለትዮሽ ወታደራዊ ቴክኒካዊ ትብብር ወቅት የተገኙ የፈጠራ ሥራ ውጤቶች እና ንብረቶች የጋራ ጥበቃ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ  በአዋጅ ቁጥር 1313/2016 አጽድቋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በፓኪስታን መንግሥት መካከል የተፈረመውን የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1312/2016 ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

በምክር ቤቱ ስብሰባ በኢትዮጵያ  መንግስት እና በሊባኖስ መንግስት መካከል በስራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ረቂቅ አዋጅ  በአዋጅ ቁጥር 1311/2016 ሆኖ በሁለት ተቃውሞ በሁለት ድምፀ- ታዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ መጸደቁን መክር ቤቱ አስታውቋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button