ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ 4ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሸ ድርድር ያለውጤት ተጠናቀቀ፣ ኢትዮጰያ ግብጽን ተጠያቂ አድርጋለች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10/2016 .ም፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረውን የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በግብጽ ሳቢያ ውጤት አለማስመዝገቡን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ያለውን ልዩነት በመፍታት ሁሉን ተጠቃሚ ያደረገ ስምምነት ለመድረስ ፍላጎት ብታሳይም ግብጽ በግድቡ ላይ እስካኹን በተደረጉት ድርድሮች ባራመደችው የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ከስምምነት ላይ ሳይደረስ ቀርቷል ብሏል።

በግድቡ የውሃ አሞላል ላይ እና በግድቡ አስተዳደር ላይ ኢትዮጵያ ለድርድር የተቀመጠችው ከሀገራቱ ጋር መተማመን ማስፈን እንጂ የሀገሪቱን በአባይ ውሃ ላይ የመጠቀም እና የመልማት መብት ለመገደብ አይደለም ሲል አቋሙን ያንጸባረቀው መግለጫው ኢትዮጵያ አሁንም በግልጽ ማስቀመጥ የምትፈልገው ዋነኛ ጉዳይ የአሁኑን እና የቀጣዩን የሀገሪቱን ትውልድ ተጠቃሚ በሚያደርግ እና የእኩልነትና ምክንያታዊነት መርሆችን ባከበረ አኳኋን የወንዙን ውሃ መጠቀሟን ትቀጥላለች ብሏል።

አራተኛው የሶስትዮሽ ድርድር መጠናቀቁን ተከትሎ የግብጽ መንግስት ያወጣውን መግለጫ የተቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመንግስታቱ ድርጅትን እና የአፍሪካ ህብረት ቻርተሮችን የጣሰ እንዲሁም የኢትዮጵያን አቋም አዛብቶ ያቀረበ ነው ሲል ኮንኗል።

የግብጽ መንግስት በበኩሉ በውሃ ሀብት እና መስኖ ሚኒስትሩ በኩል ባወጣው መግለጫ አራተኛው የህዳሴ ግድብ ድርድር ያለምንም ውጤት መጠናቀቁን አስታውቆ ለዚህም ኢትዮጵያን ተጠያቂ አድርጓል። ኢትዮጵያ ሶስቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ የቴክኒክ እና የህግ መፍትሔ ቢቀርብላትም ባለመቀበሏ አልተሳካም ሲል ገልጿል።

አለም አቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ስምምነቶችን ወደ ጎን በማለት የናይልን ውሃ በበላይነት እና ያለገደብ በመቆጣጠር ለመጠቀም ነው የምትሻው ሲል የተቸው የግብጽ መግለጫ ኢትዮጵያ ድርድሩን መሬት ላይ ያለው ነባራዊ ኹኔታ እስኪቀየር ጊዜ ለመግዛት እየተጠቀመችበት ነው በማለት ኮንኗል።

በተጨማሪም የግድቡን ውሃ አሞላልና አስተዳደር በቅርበት እንደምትከታተል በመግለጽ በግድቡ ምክንያት አንዳች ጉዳት ከደረሰባት የውሃና ብሄራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ወደኋላ እንደማትል አስታውቃለች። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button