ዜናቢዝነስ

ዜና: በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በናይጀሪያ መንግስት በሽርክና ሊቋቋም ታስቦ የነበረው አየር መንገድ አለመሳካቱ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለስልጣናት እና የናይጄሪያ አቻዎቻቸው መካከል በሽርክና የጋራ አየር መንገድን ለመመስረት ያደረጉት ውይይት አለመሳካቱ ተገለጸ።

የናይጄሪያ መንግስት ከውጭ አየር መንገድ ጋር በመተባበር በሽርክና ለመስራት አውጥቶት የነበረውን እቅድ ትቶታል ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደነገሩት አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ በዘገባው አስታውቋል።

የናይጄሪያ አየር ተብሎ ሊጠራ የታቀደው አየር መንገድ የናይጄሪያ ባለሃብቶች 46 በመቶ ድርሻ እንዲይዙ፣ የሀገሪቱ መንግስት 5 በመቶውን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀሪውን 49 በመቶ ድርሻ እንዲይዝ ታስቦ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።

ይሁን እንጂ አየር መንገዱ በአፍሪካ በርካታ መዳረሻ ማዕከላት እንዲኖሮት ለማስቻል የያዘውን  ስትራቴጂ አሁንም መቀጠሉን የዜና አውታሩ አስታውቋል።

ከናይጀሪያ አየርመንገድ ጋር የነበረው ሂደት አለመሳካት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉሪቱ ከሚገኙ አየር መንገዶች ጋር ፍትሀዊ በመሆነ ድርሻ በሽርክና ለመስራት የየዘውን ስትራተረጂ አያስቆመውም ሲሉ ስራስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹለት ዘገባው አመላክቷል።

“በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ በርካታ አየር መንገዶች ድጋፍ እንድናደርግላቸው እየጠየቁን ይገኛል፣ እያጤነውም ነው ሲሉ መግለጻቸውን ዘገባው አካቷል። የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን እንዲሁም ኢኳቶሪያል ጊኒ አየር መንገዶች እንደሚገኙበት ጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 40 በመቶ ድርሻ ያለው በቶጎ የሚገኘው አስካይ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው በሽርክና ያቋቋመው የማላዊ አየር መንገድ በጥሩ ሁኔታ እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ አስፈጻሚው እንደነገሩት አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 45 በመቶ ድርሻ ያለው የዛምቢያ አየር መንገድም በጥሩ ሁኔታ እያደገ እንደሚገኝ የዜና አውታሩ በዘገባው አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button