ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በጂቡቲ በሙቀት ምክንያት የሦስት ኢትዮጵያውያን ሕይወት አለፈ፤ ማህበሩ ለአደጋው መድረስ የአሽከርካሪ ባለንብረቶችን ከሷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13/ 2016 ዓ/ም፦ በጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የከባድ መኪና አሽርካሪዎች እና አንድ የጥገና ባለሙያ ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉንና ሁለት አሽከርካሪዎች ሆስፒታል መግባታቸው የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጸ።  

የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የአሽከርካሪ በለንብረቶች ተሽከርካሪዎቻቸው አገር ውስጥ በሚቆዩበት ወቅት ወጭ የሚያወጡ በመሆኑ ጭነት ሳይኖር ሾፌሮቹን ወደ ጁቡቲ በመላክ እዛ እንዲቆዩ ያደርጋሉ። ይህም አሽከርካሪዎቹና ረዳቶች በጂቡቲ ለላው ከፍተኛ ሙቀት ተጋላጭ እንዲሆኑ በማድረግ እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት እያደረሰ ነው ብለዋል።

አሽከርካሪዎቹ ከስራ ላለመባረር ሲሉ የሚጭኑት ጭነት ሳይኖር በባለንብረቶች ትዕዛዝ ወደ ጁቡቲ ተጉዘው በዚያ ለመቆየት እንደሚገደዱ የገለጹት አቶ ሰለሞን በሙቀት ህይወታቸው ያለፍ ውይም ጉዳት የደረሰባቸው መረጃ ያልሰጡ በርካታ አሽከርካሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረው የከባድ መኪና አሽከርካሪ ዮሴፍ ጌታሁን ተራ እስኪደርሳቸው ድርስ ከአምስት ቀናት በላይ ያለስራ እንደሚቆዩና ባለው ከፍተኛ ሙቀት ህይወት መጥፋትና ከባድ የጤና ጉዳት በአሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ መሆኑን አረጋግጧል። 

በጂቡቱ ወደብ ሙቀቱ ከ45 እስከ 50 ድግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርስ መሆኑን የገለጸው አሽከርካሪው ባሳለፍነው ግንቦት ወር የሁለት አሽከርካሪዎች ህይወት ማለፉን ገልጿል።  አንደኛው በተኛበት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል ብሏል። 

በጂቡቲና ደጋብ ሽራተን በሚባል አካባቢ ሙቀቱ እጅግ የከፋተኛ መሆኑን የገለጸው ዮሴፍ ቀድመው የገቡ ተሽከርካሪዎች ቦታ እስኪለቁና ተራቸው እስኪደርስ ድረስ ያለው መጓላላት በሙቀት ለሰዎች ህይወት መጥፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን አስረድቷል።

የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሽከርካሪዎቹ በጂቡቲ እንዲቁዩ ሲደረግ ለህይወት አደጋ ብቻም ሳይሆን ለከፍተኛ ወጭ እንደሚጋለጡ መሆኑን አስረድተዋል። ባለንብረቶቹ ተሽከርካሪዎቻቸው ጂቡቲ ከደረሱ በኋላ የሚያወጡት ወጭ አለመኖሩን የሚገልጹት አቶ ሰለሞን አሽከርካሪዎቹ ግን የኮቴ ክፍያ፣ የመኪና ማቆሚያና ሌሎች የተጋነነ ወጭ እንደሚያወጡ ተናግረዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“አሽከርካሪዎች ወደ ጁቡቲ ወደብ ሄደው በዚያ መቆየታቸው ለአገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ጉዳት አለው” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ አንድ አሽከርካሪ በቀን ቢያንስ እስከ 2 ሺህ ብር እንደሚያውጣ ጠቅሰው አስር ቀን የሚቆይ አሽከርካሪ ከ20 ሺህ ብር በላይ ውጭ እንደሚኖርበት ገልጸዋል። ይህ ብር ገቢ የሚሆነው ለጁቢቲ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰለሞን የአገሪቱን ንግድ ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት ያስከትላል ብለዋል። 

አሽከርካሪዎች የጭነቅ ቀናቸው ሳይደርስ ወደ ጁቡቲ እንዲጓዙና በዚያ እንዲቆዩ መደረጉ ከፍተኛ ህይወትና የኢኮኖሚ ጉዳት እያስከተለ በመሆኑ ባለንብረቶች ይህን ተረድተው የጭነት ቀን ሳይደርስ አሽከርካሪዎችን ቀድመው ከመላክ እንዲቆጠቡ አቶ ሰለሞን ጠይቀዋል። 

ከቅርብ ግዜ የአለም ሙቀት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመር ሲሆን በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።  ለአብነት ያህል የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ ሳዑዲ አረብያ መካ በመጓዝ በሚያደርጉት በዘንድሮው ዓመታዊው የሃጅ ስርዓት ላይ ባጋጠመ ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት 550 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧልአስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button