ዜናፖለቲካ

ዜና: ኢትዮጵያ በተለያዩ አጋጣሚዎች ችግሮች ሲገጥሙኝ ከጎኔ ሁናችሁ ደግፋችሁኛል ስትል ሩሲያን እና ቻይናን አመሰገነች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10/2016 ዓ.ም፡- ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም “ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር” በሚል መሪ ቃል በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ እየተካሄደ ይገኛል።

ከሰኔ 9 እስከ 12/2016 በሚካሔደውና ፎረሙ ላይ የታደሙት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህከ ሩሲያ ዩናይትድ ፓርቲ ምክትል የጽሕፈት ቤት ሃላፊ ክሊኖቭ አንድሬ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ አደም በውይይታቸው ላይ በኢትዮጵያና በሩሲያን መካከል ያለውን ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት ያነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ በተለያዩ አጋጣሚዎች ችግሮች ሲገጥሟት ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን ላሳየችው ድጋፍና ወዳጅነት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆን በዲፕሎማሲው ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ያነሱት አቶ አደም ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ባደረገችው ጥረትም ሩሲያ ላደረገችው ድጋፍ የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲንና መንግስቱን አመስግነዋል ።

ቀደም ሲል በሁለቱ ሃገራት የነበሩ የመንግስት ለመንግስትም ሆነ የፓርቲ ለፓርቲ ትብብሮች የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚደረግም አቶ አደም መናገራቸውን ኢዜአ ከስፍራው መረጃ ማግኘቱን ጠቅሶ ዘግቧል።

ከፎረሙ ጎን ለጎን አቶ አደም ፋራህ ከቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ የአለም አቀፍ ዘርፍ ሚኒስትር ሊዩ ጂንቻዎ ጋር መወያየታቸውንም ዘግቧል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜዎች ባጋጠሟት ፈተናዎች ሁሉ ቻይና የማይናወጥ አቋም ይዛ እያደረገች ላለው ድጋፍ አቶ አደም ምስጋና ማቅረባቸውንም ዘገባው አመላክቷል። ያመሰገኑት አቶ አደም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የፖለቲካ ወዳጅነትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውንም አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ከፍተኛ ሚና ባለው ብሪክስ አባል ሀገር ለመሆን ያደረገችው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲሳካ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲና መንግስት ላደረጉት ድጋፍም አቶ አደም ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ አደም አያይዘውም ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ስትራተጂያዊ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደምትሰራ ገልጸው ሊዩ ጂንቻዎን ጨምሮ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አመራሮች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጋብዘዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button