ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22/2016 .ም፡ አዲስ ከተዋቀሩት ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ተገለጸ።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን በምስራቅ መስቃን ወረዳ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ በሚገኙ ቤቸ ቡልቻኖ እና ምስራቅ ዲዶ ቀበሌዎች መሆኑን አስታውቀዋል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የበቸ ቡልቻኖ ቀበሌ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የታጠቁ ሀይሎች በቀበሌዋ በአንድ አከባቢ ተሰባስበው ቡና እየጠጡ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ እንደከፈቱባቸው እና አንድ እናት እና ልጇን ጨምሮ በርካቶቹ ወዲያው እንደሞቱ ገልጿል። በተጨማሪም አንዲት ነፍሰጡር የቀበሌው ነዋሪ በተተኮሰው ጥይት መቁሰሏን እና እድሜ ጠገብ የአከባቢው ሽማግሌም እግራቸው ተመትቶ መቁሰላቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

በጥቃቱ የተገደሉት በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል መወሰዳቸውን እና ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ በአዳማ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል። ጥቃቱ ዋና ኢላማ ያደረገው የማረቆ ነዋሪዎችን መሆኑን ያመላከቱት መረጃውን ያደረሱን ነዋሪው ጥቃት አድራሾቹ ወዲያውኑ ንብረትነቱ የመንግስት በሆነ ተሽከርካሪ አከባቢውን ጥለው መሄዳቸውን ተናግረዋል።   

በወረዳው በምትገኘው ሳያ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሌላ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ተጨማሪ ጥቃት የተፈጸመው በአከባቢው ከፍተኛ ዝናብ እየዘነበ በነበረበት፣ አብዘሃኛው ነዋሪ እንቅልፍ ላይ በነበረበት ወቅት እና በምሽት ጨለማን ተገን አድርገው መሆኑን ገልጸዋል።

የማረቆ ልዩ ወረዳ የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ደጋጋ እንዳሻው በርካታ ንጹሃን መገደላቸውን እና የነዋሪዎች ቤቶች መፍረሳቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል። ታጣቂዎቹ በመስቃን ወረዳ አስተዳደር የሚደገፉ ናቸው ሲሉ ኮንነዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button