ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እና የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ነዋሪዎች አስታወቁ፣ መንግስት ሁሉም ነገር ሰላም ነው ሲል አስተባብሏል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል በምትገኘው ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በፌደራል መንግስቱ ወታደሮች እና በፋኖ ሀይሎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እና የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ አራት የከተማዋ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

መንግስት በበኩሉ ሁሉም ነገር ሰላም ነው ሲል መግለጹንም አስታውቋል።

‘’በከተማዋ ከአንድ ሰዓት በፊት ውጊያ ተጀምሯል፣ ሁኔታው ስላስፈራኝ’’ ተደብቂያለሁ ሲል አንድ የላሊበላ ከተማ በስልክ እንደገለጸለት እና በወቅቱ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል።

በከተማዋ ከሚገኙ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል በአንዱ በዲያቆንነት የሚያገለግል የከተማዋ ነዋሪ በበኩሉ ከንጋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ሁሉም አከባቢዎች ውጊያው መካሄድ መጀመሩን እንደገለጸለት ዘገባው አካቷል። ሁሉም አይነት መሳሪያዎች በውጊያው ጥቅም ላይ መዋላቸውን በመኖሪያ ቦታው ንዝረት ሳቢያ መረዳቱን እንደገለጸለትም የዜናው አውታሩ በዘገባው አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button