ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ

ዕለታዊ ዜና፡ የፋኖ ታጣቂ ሀይሎች ላሊበላን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ተቆጣጠረ 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/ 2016 ዓ ም፦ የፋኖ ሀይሎች ይዘው የነበሩትን ታሪካዊቷን ላሊበላ ከተማ ትላንት ምሽት ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት ከተማዋን መቆጣጠሩን ኤፍፒ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ  ዘግቧል

በመከላከያ ስራዊት እና በፋኖ ታጠቂ መካከል ከትላንት በስቲያ ረቡ በላሊብላ ከፍተኛ ግጭት መካሄዱን እና የፋኖ ሀይሎች አበዛኛውን የላሊብላ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡

ነገር ግን ዛሬ ሃሙስ የፋኖ ታጣቂ ሀይሎች ለቀው መውጣታቸውንና የሀገር መከላከያ ስራዊት ከተማዋን መቆጣጠር መቻሉን ነዋሪ ነግሮኛል ሲል ኤፍፒ በዘገባው አመላክቷለ፡፡

ሌላኛው ነዋሪ እስከ ለሊት የፋኖ ሀይሎች አብዛኛውን የከተማዋነ አካባቢዎች ተቆጣጥርወ እንደነበርና ጠዋት ሲነሳ ታጣቂዎቹ ለቀው መውጣታቸውን ተናግሯል፡፡ “ መንገዶች ላይ የሀገር መከላከያ ስራዊት አባላት ይታዩኛል” ሲል ገልጿል።

ሁለቱም የከተማዋ ነዋሪዎች ዛሬ የትኩስ ድምፅ አለመስማታቸውን አክለው ገለፀዋል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button