ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ውለጋ እና በአርሲ ዞን በተለያየ ጊዜ በተፈጸም ጥቃት 45 አማኞች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21/ 2016 ዓ/ም፦ ባሳለፍነው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል አርሲ እና ቄለም ውለጋ ዞን በተለያየ ጊዜ በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች 45 ሰዎች ተገደሉ። ጥቃቱ ያነጣጠረው በአማኞች ላይ መሆኑን ነዋሪዎች እና ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ፣ ባሳለፍነው ሳምንት ህዳር 13 እና 17 ቀን ማንነታቸው ባልተለየ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት 36 የኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እንደተገደሉ፣ የስፍራው ነዋሪ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ነዋሪው በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ህጻናት እና አዛውንቶች ይገኙበታል ብለዋል።  

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ጥቃቱን የፈጸመው፣ መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ የሚጠራው ዐማፂ ኃይል መሆኑን ገለጸው በጥቃቱም 27 ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል፡፡ ኃላፊው ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው፣ባሳለፍነው ሳምንት ቡድኖ በድሌ ዞን ጫዋቃ ወረዳ ላይ የመንግስት ሀይሎች የወሰዱበትን እርምጃ ለመበቀል ብሎ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ሀይላችን በአከባቢው ላይ ህዳር 13 እና 17 ቀን አድርሷል የትባለውን ጥቃት አልፈጸመም ሲሉ የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል፡፡ 

ህዳር 14 በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ተገድለዋል። የጥቃቱ ሰለባ የተደረጉት ምዕመናኑ  በመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ጸሎት እያደረጉ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተወስደው ዘጠኙ ተገድለው መገኘታቸውን ቢቢሲ ዘገቧል። 

የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የወነጌል ማህበር የቲዎሎጂ ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር ለሊሳ ኤሊያስ ከተገደሉት መካከል የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎችም ጭምር እንደሚገኙበት የገለጹ ሲሆን የጥቃት አድራሾቹ ማንነት እንዳልታወቅ ጠቅሰዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button