ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአማራ ክልል በሚፈጽም የአየር ጥቃት የዜጎች ህይወት መጥፋት እና የመሰረተ ልማት ውድመት ቀጥሏል

አዲስ አዲስ፣ ህዳር 25/ 2016 ዓ/ም፦ ባሳለፍነው ሳምንት በአማራ ክልል በርካታ ወረዳዎች በተፈፀመ የከባድ መሳሪያ እና ድሮን ጥቃት የሰዎች ህይወት ሲጠፋ ወሳኝ የሆኑ መሰረተ ልማቶች ላይም ውድመት ድርሷል። የአይን ዕማኞች ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት በተፈጸመው ጥቃት በመኖሪያ ቤቶች እና መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ወገልጤና ከተማ ሃሙስ ወድ 5 ሰዓት አካባቢ አስፈላጊ የሆኑ የሀከመና ቁሳቁስ የጫነ አምቡላንስ ከደሴ ከተማ ወደ ደላንታ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል በመጓዝ ላይ እያለ በከተማዋ እንደደረሰ በተፈጸመ የአየር ጥቃት በተሽከርካሪው ላይ ጉዳት ሲደረስ የሰዎች ህይወትም አልፏል። ወንድሙ የተገደለበት የወገልጤና ከተማ ነዋሪ ለአዲሰ ስታንዳርድ እንደተናገረው በጥቃቱ ሄኖክ ሹሜ የተባለ ወንድሙን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገድለዋል።

“በተሽከርካሪ ውስጥ ወንድሜን አስክሬን ሳየው መለየት በማይቻልበት ሁኔታ ነበር የተጎዳው” ሲል የገለጽው የሄኖክ ወንድም፣ የተቶካሹ ሃይል አንቡላንሱን በከባዱ መጉዳቱ ለመለየት ይሚያስችል ነገር ምንም አልነበረም ብሏል። 

ወንድሙ እንደሚለው ሄኖክ በደላንታ የመጀመሪያ ሆስፒታል ውስጥ ለበረካታ አመታት የፋርማሲ ባለሙያ ሆኖ ያገለገል ሲሆን በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የተኛውም ታጣቂዎች ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የለውም። “ይህ ያልታሰበ አደጋ ሁሉንም የቤተሰብ አባላትን ያስደነገጠ እና ትልቅ ሀዘን ውስጥ የከተተ ነው”ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ በዚያው በሰሜን ወሎ ዞን፣ ባለፈው ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በሐብሩና ላስታ ወረዳ በወደቀ የከባድ መሣሪያ ጥይት የንጹሃን ህይወት ማለፉን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል። ላስታ ወረዳ ወደ 5 ሰዓት ሲሆን በገበያ አካባቢ በተፈጸመ ከባድ መሳሪያ ጥቃት የህጻናት፣ እናቶችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል። 

መንግስት በአማራ ክልል በጥቅምት ወር በወሰደው የአየር ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የተባሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል። ድርጅቱ ህዳር 7/ 2016 ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ ኢላማ ከተደረጉ ቦታዎች ማካከል ትምህርት ቤትና መነሃሪያ ይገኝበታል ሲል ገልጿል፡፡

በመንግስት እና በፋኖ ታጣቂ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት በክልሉ ወሳኝ መሰረተ ለማቶች ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። በተለይ ባህርዳርን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው አንጋሳ ድልድይ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በቅርቡ የአማራ መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጋሻው አዋኬ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት ባህር ዳር፣ ሞጣ፣ መካነሰላምን እና በአዲስ አበባን የሚያገናኘው 40 ሜትር ርዝመት ያለው ድልድይ ላይ ጉዳት ደረሷል። አቶ ጋሻው ድልድዩ ከአራት አስርት አመታት በፊት የተገነባ ቢሆንም ጉዳት እስከደረሰበት ግዜ ድረስ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር  ብለዋል። 

ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ የክልሉ መንግስት ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት በንቃት እየሰራ መሆኑን አቶ ጋሻው ገልጸዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button