ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ከ16 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለፈተና ይቀመጣሉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12/2016 .ም፡ ከ16 ሺህ በላይ የከተማ አስተደደሩ ሠራተኞች ዛሬ አርብ ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፈተና እንደሚቀመጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ፈተናውም በሶስት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ እንደሚሰጥ ጠቁሟል። ፈተናውም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በከተማው በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በዛሬው ቀን ታህሳስ 2/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ 7 ስዓት ጀምሮ እንደሚሰጥ አመላክቷል።

ቢሮውም ይህንን ያስታወቀው ከ11ዱ ክፍል ከተሞች ከተውጣጡ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ከስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ከተመረጡ 16 ተቋማት ሃላፊዎች ጋር የሰራተኞች መመዘኛ ፈተና አሰጣጥ አስመልክቶ ትላንት ታህሳስ 11 ቀን 2016ዓ.ም ባካሄደው ኦረንቴሽን እና ውይይት ላይ ነው።

በእለቱ የፈተና አሰጣጥ ቅድመ ሁኔታዎች እና ሂደቶችን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጣሰዉ ገብሬ (ዶ/ር) ገለጻ ማድረጋቸውን ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

ኃላፊው እንዳሉትም ከሆነ ፈተናውም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በከተማው በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዛሬ ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ 7 ስዓት ጀምሮ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

በፈተናው ወቅትም ምንም አይነት የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር ቢሮው ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እንዲሁም ከፀጥታ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት ኃላፊው የመንገድ ትራንስፖርት ፍሰቱን እና የትራንስፖርት ስምሪቱን ለማሳለጥ ከከተማዋ ትራፊክ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ጥረቶች መጀመራቸውን እና በተመሳሳይም ለተፈታኞች በቂ የትራንስፖርት ስምሪት ስራ እንደሚከናወንም ጭምር አስገንዝበዋል።

ኃላፊው አክለውም አጠቃላይ አመራሩ ስለ ፈተናው እና የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ የሚገኙ አሉባልታዎችን በትክክለኛ መረጃ በመቀልበስ ተፈታኞችን የማረጋጋት ስራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button