ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ በነበረው ግጭት ከ80 በላይ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ተገድለዋል – ኢሰመጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል በነበረ ግጭት ከ80 (ሰማንያ) በላይ የሆኑ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ከግድያው በተጨማሪ የአካል ጉዳት፣ ድበደባ፣ ማስፈራራትና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ብሏል።

ለግድያው ዋነኛ ምክንያት በግጭቱ ወቅት የነበረው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መሆኑን የጠቆመው ኢሰመጉ በተጨማሪም ቤት ለቤት በመዘዋወር ግድያ መፈጸሙን ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቁሟል።

ከጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሟቾች አስክሬን በመርዓዊ ከተማ ማሪያም ቤተክርስቲያን በጅምላ ቀብር መፈጸሙን እና በከተማዋ የተፈጸመውን ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪ አካባቢውን ለቆ እየወጣ ሆኑን ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን አስታውቋል።

የተዘረዘሩትን ጉዳዮች በአካል በመገኘት ምርመራ በማድረግ ለማረጋገጥ አለመቻሉን አመላክቷል።

በክልሉ በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ አካላት በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸውን ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ ከመፈጸም እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል።

በመርአዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ እኩለቀን ድረስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በታጣቂዎች መካከል በተካሄደው ውጊያ ከ100 ሰዎች በላይ ተገድለዋል ሲሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የከተማዋ ነዋሪ መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በከተማዋ የተፈጸመው ጅምላ ግድያ ነበር ሲሉ ነዋሪዎች መግለጻቸውመ በዘገባው ተካቷል። በከተማዋ በምትገኘው የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ብቻ 50 የሚጠጉ ሰዎች አስከሬን መቀበሩን ነዋሪዎቹ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button