ዜናጤና

ዜና፡ በአማራ ክልል አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ሰዎች የኮሌራ በሽታ ክትባት እንደተሰጣቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አዳጋች ቢሆንም በክልሉ ለሚኖሩ አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ለሚጠጉ ነዋሪዎች የኮሌራ ክትባት መስጠቱን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት ክልሉ በርካታ አደጋዎችን በማስተናገድ ላይ እንደሚገኝ የጠቆመው የአለም የጤና ድርጅት ዋነኛዎቹም ድርቅ፣ ኩፍኝ፣ ወባ እና ኮሌራ ወረርሽኝ መሆናቸውን አስታውቋል።

በአማራ ክልል በፌደራል መንግስቱ የጸጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት ሳቢያ በከፍተኛ ቁጥር የክልሉ ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው በመሰደድ ላይ መሆናቸውን ያስታወቀው ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት 800ሺ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ጠቁሟል፤ ከእነዚህ ውስጥ 12 በመቶ የሚሆኑት በ40 የክልሉ መጠለያ ካምፖች እንደሚገኙ አመላክቷል።  

የአለም የጤና ድርጅት ለክልሉ የጤና ቢሮ እና መሰል ተቋማት የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፣ ከአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን በላይ የክልሉ ነዋሪዎች በአፍ የሚወሰድ የኮሌራ ወረርሽኝ ክትባት መስጠቱንም ገልጿል። በክልሉ ዘጠኝ ቦታወች ከፍተኛ አደጋ የተደቀነባቸው ተደርገው መለየታቸውነ የጠቆመው ድርጅቱ የጸበል ውሃ የሚገኝባቸው ቦታዎች፣ ተፈናቃዮች የተጠለሉባቸው ካምፖች፣ ስደተኞች የሚገኙባቸው እንደ መተማ እና ቋራ የመሳሰሉ ከተሞች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

በክልሉ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል ሞጃና ወደራ በምትባል ወረዳ ክትባቱን መስጠት ተቸግሮ እንደነበር የጠቆመው የአለም የጤና ድርጅት ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ወረዳዋ በመንግስት ቁጥጥር ስር ስላልነበረች እና በፋኖ ታጣቂዎች ተቆጣጥረዋት ስለነበር መሆኑን ጠቁሟል፤ በወረዳዋ በተሰማሩ የጤና ቡድኑ አባላት እና በፋኖ ታጣቂዎቸ መካከል በተካሄደ ስኬታማ ድርድር 98 ነጥብ 5 በመቶ ለሚሆኑ የወረዳዋ ነዋሪዎች ክትባት መስጠት መቻሉን አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button