ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የአለም ባንክ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27/2016 ዓ.ም፡- የአለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቤገርዴ እና የባንኩ የደቡብ እና ምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ ከዛሬ ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ የገንዘብ ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ያጋራው መረጃ ያሳያል።

የባንኩ ሀላፊዎች የጉብኝታቸው ዋነኛ አላማ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማገዝ እና በባንኩ እና በሀገሪቱ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ሚኒስቴሩ በመረጃው አመላክቷል።

የባንኩ ሀላፊዎች በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች እና በሀገሪቱ ከሚገኙ የልማት አጋር ድርጅቶች ሃላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ሃላፊዎቹ በቆይታቸው የከተማ ሴፍቲኔት ውጤታማናትን እና የስራ ፈጠራ ፕሮጀክቶች ባሉበት አከባቢ በመገኘት የፈጠሩትን እድል እንደሚጎበኙ ተመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button