ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ አንቶኒ ብሊንከን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ለጠ/ሚኒስትር አብይ ደውለው እንደነገሯቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18/2016 ዓ.ም፡- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ማውራታቸው ተገለጸ። አንቶኒ ብሊንከን ከዶ/ር አብይ ጋር ባደረጉት ውይይት አሜሪካ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባት መግለጻቸውን የቃል አቀባይ ቢሯቸው መግለጫ አስታውቋል።

አንቶኒ ብሊንከን የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ችግሮችን ለመፍታት ዋነኛው መንገድ ሰላማዊ አማራጮችን መከተል ብቻ ነው እንዳሏቸው የጠቆመው መግለጫው የፖለቲካ ውይይት እና ሰብአዊ መብትን ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋቸዋል ብሏል።

የእርዳታ አቅርቦቱን ለማስጀመር የሚያስችል የተሻሻለ ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ በሁለቱ ውይይት መነሳቱን የቃል አቀባዩ መግለጫ አመላክቷል። ቀና፣ እውነተኛ እና ሁሉን አሳታፊ የሆነ የየሽግግር ፍትህን ለማስፈን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ ናቸው ሲሉ ሃላፊው ለጠ/ሚኒስትሩ እንደገለጹላቸው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ቢሮው ያወጣው መግለጫ አካቷል።

በተመሳሳይ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሃፊ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በኢትዮጵያ ሰላም፣ ብፅግናና መረጋጋት ላይ ያተኮረ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ማስታወቁን መዘገቡ ይታወሳል።

ብሊንከን  በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ማቆም ስምምነትን በመተግበር ረገድ መሻሻል መኖሩን ጠቁመው በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ሁኔታ ግን እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን እንዲሁም ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምግብ ዕርዳታን በፍጥነት ለማስጀመር የጋራ ግብን ለማሳካት የሰብአዊ ርዳታ ስርጭት ስርዓትን በተጠናከረ ሁኔታ ለመዘርጋት ያለመ ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ መጥቀሱም በዘገባው ተካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button