ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ለዳሬሰላሙ የሰላም ድርድር አለመሳካት ተጠያቂው መንግስት ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11/2016 ዓ.ም፡- ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) መካከል በታንዛንያ ዳሬሰላም ሲካሄደ የቆየው የሰላም ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን መንግስት አስታውቋል። ለድርድሩ አለመሳካት በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) ተጠያቂ አድርጓል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) ማምሻውን በቃል አቀባዩ በኩል ባጋራው መግለጫ በበኩሉ ለድርድሩ አለመሳካት መንግስትን ተጠያቂ አድርጎ በዳሬሰላም ተፈጥሮ የነበረውን ክልሉን ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ በመውሰድ እምርታ ሊያስመዘግብበት የሚያስችለውን ታሪካዊ እድሉን የኢትዮጵያ መንግስት አልተጠቀመበትም ሲል ኮንኗል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የአዲስ ስታንዳርድ ምንጮች ተደራዳሪዎቹ ከትላንት ጀምሮ በቁልፍ ጉዳዮች ዙሪያ የነበራቸውን ልዩነት ማጥበብ አለመቻላቸውን ገልጸዋል።

በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪዎች በኩል የቀረበው መደራደሪያ ነጥብ በመንግስቱ አወቃቀር ዙሪያ ትልቅ ለውጥ እንዲደረግ የሚጠይቅ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቻችን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ሁሉን አቀፍ መንግስት ማቋቋም የሚለው እንደሚገኝበት አመላክተዋል።

በዚሁ ነጥብ ላየ የመንግስት አቋም ከቡድኑ ጋር በተናጠል እና ለብቻ በመሆን ነገሮችን ማስተካከል የሚል መሆኑን ነግረውናል። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ልክ እንደ ፕሪቶርያው የፌደራል መንግስቱ እና የህወሓት ስምምነት ሁሉን ያሳተፈ መንግስት እንዲመሰረት መጠየቁን አስታውቀዋል።

በመንግስት በኩል ተደራዳሪ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን በማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ገጻቸው ገለጻ ስምምነቱ ያልተሳካው በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግትር አቋም ነው። ቡድኑ በበኩሉ ለድርድሩ አለመሳካት መንግስትን ተጠያቂ አድርጓል፤ የፌደራል መንግስቱ መሰረታዊ የክልሉን ችግር ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ የቡድኑን ከፍተኛ አመራሮች ሹመት መስጠት ላይ ትኩረት አድርጓል ሲል ተችቷል።

ቡድኑ ማምሻውን ባወጣው መግለጫው ከፍተኛ አመራሮቹን ለድርድሩ ስኬት ሲል ማሳተፉን አስታውቆ ከዛንዚባሩ የድርድር ወቅት ጀምሮ እስከ ዳሬሰላሙ የአሁኑ ውይይት ድረስ ወነኛ የክልሉ ችግሮችን በመለየት እና ሁሉን የሚያሳትፍ የመደራደሪያ ነጥቦች በማድረግ የክልሉ ችግሮን ትርጉም ባለው መልኩ እንዲፈቱ ለማድረግ መጣሩን አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በኢትዮጵያ መንግስት ምክንያት ክልሉን ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ በመውሰድ እምርታ ሊያስመዘግብበት  የሚያስችለውን ታሪካዊ እድሉን አልተጠቀመበትም ሲል ኮንኗል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ይዞት በወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) በዳሬሰላሙ ድርድር ይዟቸው ይቀርባሉ ብሎ መንግስት ጠብቆ የነበረው ነጥቦች ሀገሪቱ ከደረሰችበት ምዕራፍ ጋር የተጣጣማሉ ብሎ ነበር ሲል ገልጾ ነገር ግን በዳሬሰላሙ ድርድር ቡድኑ ይዞት የቀረበው የድርድር ነጥብ “መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ” የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ነው ሲል ተችቷል።

መንግስት በመግለጫው የሽብር ቡድኑ ሲል የጠራው በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት ታይቷል ብሏል። በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መርጧል ሲል ቡድኑን ኮንኗል።

የኢፌዴሪ መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሔ ያለው አቋም እንደተጠበቀ ሆኖ ሕግና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የማስከበር ተልዕኮውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

ውይይቱ እንዲሳካ ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርቧል።

ከወራት በፊት በታንዛንያ ዛንዚባር ውይይት ተካሂዶ እንደነበር ያወሳው የመንግስት መግለጫ በወቅቱ ስምምነት ላይ ያልተደረሰው በቡድኑ ምክንያት ነው ሲል ገልጿል።

ከአምስት አመታት በፊት በሀገሪቱ ለውጥ በመጣበት ወቅት የተመለሱ ጉዳዮችን ከማነብነብ ውጭ የሚቆጠርና የሚቋጠር አጀንዳ ማምጣት ባለመቻሉ የዛንዚባሩ ድርድር በመንግስት ይሁንታ ተቋርጦ እንዲቀጥል ተደርጓል ሲል አትቷል።

በዛንዚባሩ ውይይት በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በኩል ከ60 ዓመታት በፊት የኦሮሞም የሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችም ሁሉ ጥያቄዎች የነበሩና ተመልሰው ያደሩ ጥያቄዎችን አንስቷል ብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button