ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው ከተያዙ ዜጎች በቂ ማስረጃ ያልተገኘባቸው እንዲለቀቁ ምክረ ሃሳብ አቅርበናል- መርማሪ ቦርዱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3/ 2016 ዓ.ም፡- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው የተያዙ ዜጎች የምርመራ ሂደት በማፋጠን ክስ እንዲመሰረት፣ በቂ ማስረጃ ያልተገኘባቸው እንዲለቀቁ፣ ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልጋቸው በቂ ዋስትና አቅርበው እንዲለቀቁ ለኮማንድ ፖስቱ ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አስታውቋል፡፡

መርማሪ ቦርዱ ይህን ያስታወቀው በትላንትናው እለት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው በተያዙ ዜጎች ላይ ባደረገው የመስክ ምልከታ ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ አለመኖሩንም መረጋገጡን ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡

ምክረ ሃሳቦች ሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል፣ ጥቆማ የቀረበባቸው የተጠርጣሪ ማቆያ ቦታዎችን መጎብኘት፣ የሚመጡ ተጨማሪ ጥቆማዎችን ማጣራትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ መወያየት የቀጣይ ሥራ መሆኑንም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አዝመራ አንደሞ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባና በአማራ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው የተያዙ ዜጎች ጋር በተያያዘ እስካሁን በተደረገው ማጣራትም በኮምቦልቻ፣ በጎንደር፣ በባሕርዳር፣ በሸዋ ሮቢት እና በአዋሽ አርባ በሚገኙት ማቆያ ማዕከላት ብቻ 764 ተጠርጣሪዎች በሕግ ጥላ ሥር እንደሚገኙ ማወቅ እንደተቻለ ሰብሳቢው ገልጸዋል።

መርማሪ ቦርዱ በአዲስ አበባና በአማራ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው የተያዙ ዜጎች የሚገኙባቸውን ማዕከላት ላይ በተደረገው የመስክ ምልከታ ከተጠርጣሪዎች ጋር በቡድንና በተናጠል በተደረገ ውይይት የሕክምና፣ የምግብ፣ የጽዳትና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን በተሻለ ሁኔታ እያገኙ ስለመሆናቸው እንዳረጋገጡላቸው አመላክተዋል ብሏል።

ማጣሪያ በተደረገባቸው ማዕከላት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የታሰሩ ግለሰቦች ስም ዝርዝር፣ ብዛት የታሰሩበት ቦታና ምክንያት ማወቅና መለየት እንደተቻለም ተናግረዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ትላንት ባውጣወ መግልጫ የማገቻ ካምፕ እንደሌለው፣ ነገር ግን ዕዙ ያዘጋጃቸው ማቆያ ስፍራዎች እስካሁን አምስት ብቻ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡

የተለያዩ ፎቶዎችን እየለጠፉ ‘‘የሕጻናትና የዐዋቂዎች የማገቻ ካምፖች ናቸው’’ የሚባሉት ቦታዎች ፈጽሞ እውነት ያልሆኑ የፈጠራ ዜናዎች ናቸው ሲል የሚነሱበትን ጥሬታዎች አስተባብሏል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button