ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግስት ውይይት በቀጣይ ሳምንታት የመቋጨት እድል ይኖረዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2/2016 .ም፡ የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ልዑካን ከመስከረም 16 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ጉብኝት ማካሄዳቸውን እና ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የገንዘብ ተቋሙ የኢትዮጵያ ዋና ሃለፊ በሆኑት በአልቫሮ ፒሪስ የተመራው ልዑክ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ያካሄደው ውይይት ዋነኛ አጀንዳ መንግስት ለሚያካሂደው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፍ እንዲደረግለት መጠየቁን ተከትሎ መሆኑን መግለጫው አመላክቷል።

በመስከረም ወር አጋማሽ ከተካሄደው ውይይት በተጨማሪ ባሳለፍነው ሳምንት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር የገንዘብ ተቋሙ ባለስልጣናት በሞሮኮ ማራካሺም ውይይት ማካሄዳቸውንም ጠቁሟል።

በአዲስ አበባ እና በማራካሺ በተካሄዱት ውይይቶች የተደረሰ ስምምነት መኖሩንም ይሁን አለመኖሩን ተቋሙ ያለው ነገር የለም።

ከመንግስት ጋር የተካሄዱትን ውይይቶች ተከትሎ የቡድኑ መሪ የኢትዮጵያ ዋና ሃለፊ በሆኑት አልቫሮ ፒሪስ ባወጡት መግለጫ ቡድኑ ሀገሪቱ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እየወሰደችው ያለውን እርምጃ አድንቋል። ይህንንም ለማድረግ ያስቻላት አስፈላጊ የሆነ ጥብቅ የበጀትና የገንዘብ ፖሊሲ ማስፈጸሟ ነው ሲል ገልጿል። ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ እርምጃዎቹ ወሳኝ መሰረት የሚጥሉ ናቸው ሲል አወድሷል።

ልዑኩ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ባካሄደው ውይይት አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋሙ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ለማገዝ የሚያስችል ጥሩ መሻሻል የታየበት ውይይት አካሂደናል ብሏል። መንግስት ለተያያዘው የኢኮኖሚ ፕሮግራም የሚያስፈልጉ ማሻሻያዎች ዙሪያ የሚካሄደው ውይይቱ በቀጣይ ሳምንታትም እንደሚቀጥል እና ከስምምነት ላይ ይደረሳል የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል።

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ቀናት አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በሞሮኮ ማራካቺ ከተማ አመታዊ ስብሰባ ማካሄዳቸው ይታወቃል። የሁለቱ የገንዘብ ተቋማት ስብሰባ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የብድር ሸክም ያጎበጣቸውን ሀገራት መታደግ ዋነኛ አጀንዳቸው መሆኑን ሮይተርስ የዜና ወኪል ባስነበበው ዘገባው አስታውቋል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብጽ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ሊባኖስ፣ ቱኒዝያ፣ ፓኪስታን፣ ስሪላንካ፣ ዩክሬን እና ዛምብያ የሁለቱ የገንዘብ ተቋማት ትኩረት ሰጥተው የሚመክሩባቸው መሆኑን የዜና አውታሩ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኢትዮጵያን አስመልክቶ የዜና አውታሩ ባቀረበው አጭር መግለጫ የሀገሪቱ የብድር እዳ የተከማቸው በዋነኝነት የኮቪድ ወረርሽ ያሳረፈው የኢኮኖሚ ጫና እና በትግራይ የተካሄደው እና ለሁለት አመታት የዘለቀው ጦርነት መሆኑን አስታውቆ የአሜሪካ መንግስት በሀገሪቱ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ  ከቀረጽ ነጻ መብቶችን በማንሳቱ መሆኑን በዘገባው ተመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button