ዜና: በአስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ የተከሰሱ 13 ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ አቀረቡ
ማህሌት ፋሲል
ታህሳስ 01/2012 – በኢተማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን የግል አጃቢ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ና 12 ተከሳሾችህገ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በጉልበት ለመናድ በሚል ለቀረበባቸው ክስ ዛሬ ረፋዱ ላይ የክስ መቃወሚያ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የሚታይበት 1ኛ ችሎት ቀርበው 19 ገፅ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ፡፡
ህዳር 12/2012 ዓ.ም ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በጉልበት ለመናድ በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 13 ተከሳሾች በከፍተኛ አጀብ ወደ ፍርድ ቤት የመጡ ሲሆን የቃል አቤቱታቸውን ለችሎት አሰምተዋል ፡፡
12ኛ ተከሳሽ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አ.ብ.ን) የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ክርስቲያን ታደለ የአራዳ መጀመሪያ ፍርድ ቤት መስከረም 7 እና 10/2012 ዓም በዋለው ችሎቱ የኤሌክትሮኒክስ ንብረቶችን እንዲመለስልን ትእዛዝ ሰቶ የነበረ ቢሆንም የአዲስ አበባ ፖሊስ እስካሁን ሊመልስልን አልቻለም ፡ ህዳር 12 ወደ ማረሚያ ቤት ልንወርድ ስንል ስለ ንብረታችን ስንጠይቅ ድብደባ ፈፅመውብናል ፡ እኛ ከታሰርን በሕዋላ በንብረቶቻችን ወንጀል እተሰራባቸው ነው ፡ ወደ ማረሚያ ቤት የወሰዱንም ለሊት ላይ ነው ሲል ለችሎት አሰረድቷል፡፡ ተከሳሹ አያይዞም በአለርት ሆስፒታል ህክምና የተከታተለ የነበረ ሲሆን ወደ ቂልንጦ ማረሚያ ቤት ከመጣ በውላ እንደተቋረጠበትችሎተ ችሎት ተናግሯል፡፡
አንደኛ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በጠበቆች በኩል ህክምና ማግኘቱ ስለቋረጠ ጤንነታቸው በተለይ አንደኛው እግራቸው ወደ ሽባነት እየሄደ ነው ፡ ህክምና እንዲያገኙ ሲሉ ጠበቆች ለችሎት ተናግረዋል፡፡ ጠበቆች አክለውም እኛ እና ደንበኞቻችን የምንቀባበለው መረጃ በማረሚያ ቤቱ ሳንሱር ሳይደረግ የለፍልን ሲሉ ለችሎት ተባግረዋል፡፡
13ተኛ ተከሳሽ በለጠ ካሳ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ማረሚያ ቤቱ በቤተሰብ ጥየቃ ወቅት ሰአቱን እንቀነሰባቸው እና ትኩስ ነገር እንደ ቡና እና ሻይ ያሉ እንዳይገቡልን ተከልክለናል ሲሉ አቤቱታ ኣቅርበዋል ፡፡ ፖለቲከኞች እንደመሆናችን መፅሀፍ እንዲገባልን ይፈቀድልን ፡ ተከሰን ያለነው ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በጉልበት ለመናድ በሚል ወንጀለል ሲሆን ምንም አይነት አቤቱታን ስንፅፍ ግን ማረሚያ ቤቱ በፀረ ሽብር የተከሰስን ብላችሁ ፃፉ ነው ሚለን ሲል ለችሎት ተናግሯል፡፡
ችሎቱም ተከሳሾች የተከሰሱት ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በጉልበት ለመናድ በሚል ወንጀል እንጂ በፀረ ሽብር ስላልሆነ ማረሚያቤቱ እንዲያስተካክል እንዲሁም ህክምና እንዲያገኙ ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን የአቃቤ ህግ የመቃወሚያ መልስ ለመቀበል እና በኤሌክትሮኒክስ ንብረቶቻቸውና በመፀሀፍ አቤቱታዎች ላይ ምላሽለ ለመስጠት ለታህሳስ 21 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል፡፡ አስ