ዜናፖለቲካ

ዜና: "ሁለቱም ጋር ሃዘን አለ፣ እስካሁን የነበረው ችግር በዚሁ ይብቃ” - የኦሮሞ እና የአማራ ማህበረሰብ ተወካዮች በሸዋሮቢት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በይፋት ቀጣና እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች “መንግስት ነፃነትን ያውጅልን ወደቀያችን እንገባለን” ሲሉ ጠየቁ።

ይህንን የተናገሩት በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በኤፍራታና ግድም ወረዳ ጀውሃ ቀበሌ ላይ የአጎራባች ወረዳ ማለትም የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ቀበሌዎች ከከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና የዞን አመራሮች እንዲሁም የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ተገኝተው ባደረጉበት የምክክር መድረክ ነው።

በዚህ መድረክ ከጀውሃ እና ከአዲስ ዓለም ነጌሶ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በሸዋሮቢት ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በምክክር መድረኩ መገኘታቸውን ከአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለበርካታ ዘመናት የኦሮሞ እና የአማራ ማህበረሰብ አብሮ ኖሯል ሲሉ ገልጸው ከስድስት ዓመታት ወዲህ ግን ሰው በብሔሩ ተፈልጎ ሞቷል፤ ሃብት ንብረቱ ወድሟል፤ “ሁለቱም ጋር ሃዘን አለ እስካሁን የነበረውን ችግር በዚሁ ይብቃ ለአብሮነታችን በጋራ እንስራ የወደፊቱ ይበልጣ እና” በማለትም ተናግረዋል።

አማራ ጠል አልያም ኦሮሞ ጠል የሆነ ከጭንቅላቱ ያውጣ ወንድማማችነን ጎረቤት ነን በየቀያችን ሰርተን መለወጥ እንፈልጋለን ብለዋል የሁለቱም ብሔረሰብ ተሳታፊዎች።

የአማራና የኦሮሞ ማህበረሰብ እርስ በእርሱ የተሳሰረ፤ የረጅም አመት የአብሮነት ባህል ያለው ህዝብ መሆናቸውን በመግለጽ  ችግሩ ያለው ማህበረሰቡ ጋር አይደለም፣ የአመራሩ እና የዘመኑ የፖለቲካ ስብራት ነው “መንግስት ስርዓቱን ያጥራ” በሰላም ሃብት ንብረት በአካባቢያች ማፍራት እንፈልጋል ብለዋል።

የከፍተኛ መከላከያ ሰራዊት አመራሮችም በሁለቱም ብሄር ሰም ለሚነግዱ ፅንፈኛ ማህበረሰቡ ምሽግ መሆን የለበትም እስከዛሬ በሁለቱም በኩል ምሽግ በመሆን ማህበረሰቡ ለጥፋት ተዳርጓል “ነፃነት ያለው ህዝቡ ጋር” ያ ማለት ጥፋተኛን ለህግ ካጋለጠና ከሰጠ ቀጣናው ሰላም ይሆናል በማለት አስረድተዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የሰ/ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ በበኩላቸው የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች ወደቀያቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተው የህግ የበላይነት መከበር እንዳለበትና ለጀውሃ ቀበሌ የፀጥታ ችግር ግንባር ቀደም ተዋናይ የነበሩ አጥፊዎች በህግ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው አበክረው እንደሚሰሩና ፤ በጀውሃና በአዲስ ዓለም ነጌሶ ቀበሌዎች የሚገኙ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በቅርብ ቀናት ይጀምራሉ ነው ያሉት።

በኤፍራታና ግድም ወረዳ የጀውሃ ቀበሌ በተያዘው በጀት ዓመት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ትምህርት ቤት እና የጤና ጣቢያን ጨምሮ የመንግስት ተቋማት ዝግ ሆነው መቆየታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽ መረጃ አመላክቷል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button