ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዕለታዊ ዜና፡ በትግራይ ጦርነት ወቅት የተሰዉ የክልሉ ተዋጊዎች በትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰማዕትነት ክብር እንዲሰጣቸው መንበረ ሰላማ ውሳኔ አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25/2016 .ም፡ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል ለሁለት አመታት በዘለቀው ደም አፋሳሽ ጦርነት ወቅት የተሰው የክልሉ ተዋጊዎች የክብር ሰማዕትነት ተሰጥቷቸው፣ “የእግዚአብሔር ሀገር ቅድትስ ትግራይ ሰማዕታት” ተብለው እንዲጠሩ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ላዕለዋይ ቤተክህነት ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ።

ውሳኔው የተላለፈው የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሊቃነ ጳጳሳት፣ ስራ አስፈጻሚ እና የመላ የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ላዕለዋይ ቤተ ክህነት መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው አለም አቀፍ መንፈሳዊ ጉባኤ መሆኑን አመላክቷል።

“በትግራይ በተካሄደው የዘር ማጥፋት ጦርነት ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው ክብር ሲሉ የተሰዉ የትግራይ ጀግኖች የክልሉ መንግስት የሰማዕታቱን ክብር የሚመጥን ክልላዊ ሀዘን ማወጁ ይታወቃል” ያለው የክልሉ የቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት መግለጫ፣ ይህንንም ተከትሎ በመንበረ ሰላማ ስር በሚተዳደሩ አብያተ ክርስትያናት ሁሉ ክብሩ እንዲሰጣቸው እና እንዲተገበር አሳስቧል።

በተጨማሪም ሰማዕታቱ በጦርነቱ ወቅት አንዲት ህይወታቸውን ለትግራይ የሰጡ ስለሆኑ ዜና እረፍታቸው ከተሰማበት ጀምሮ ሁልጊዜ በሚኖር የፍትሓት ስነስርአት ያለምንም ክፍያ ፍትሓተ ጸሎት እንዲደረግላቸው ሲል ውሳኔ መተላለፉን መግለጫው አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button