ዕለታዊፍሬዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዕለታዊ ዜና፡ በአማራ ክልል እየተስፋፋ ባለው የኮሌራ ስርጭት በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ የ76 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23/ 2016 ዓ.ም፡- በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ታጠቂ ሀይሎች መካከል ግጭቶች እየተካሄዱ ባለበት እንዲሁም በዝናብ እጥረት ሳቢያ ከ 1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስከኳይ ድጋፍ በሚሹበት አማራ ክልል የተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረርሽኝ ከሐምሌ 8/2015 ዓ.ም ጀምሮ በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ የ76 ሰዎች ህይወት መንጠቁን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በግጭት እና በድርቅ እየተፈተነ በሚገኘው አማራ ክልል “የኮሌራ ወረርሽኝ ስርጭት እየሰፋ መምጣቱን” የገለፁት የኢንስቲትዩቱ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር አብርሃም አምሳሉ አሁን ላይ 31 ወረዳዎችን በማዳረስ 4 ሺህ 84 ሰዎች እጥቅቷል ብለዋል፡፡ ካለፉት ሦስት ቀናት ጀምሮ በደብረ ብርሃን ከተማ በሽታው ተከስቷል ሲሉ አክለው ገልፀዋል፡።

በስታው በቋራ ወረዳ በመነሳት ወደ ባሕር ዳር ዙሪያ፣ ደራ፣ ምሥራቅ ደንቢያ፣ አለፋ፣ ምዕራብ በለሳ፣ ጎንደር ከተማ፣ ጃንአሞራ እና በመሳሰሉ የክልሉ ምዕራባዊ አካባቢዎች እየተስፋፋ መምጣቱን  ዳይሬክተሩ አብርሃም አምሳሉ ገልፀዋል፡፡

በሽታው ከተከሰተባቸው 31 ወረዳዎች ውስጥ በክትባት አቅርቦት እጥረት ምክንያት ሥርጭቱ ጎልቶ በታየባቸው ሰባት ወረዳዎች እና በሁለት ከተማ አሥተዳደሮች ብቻ ክትባቱ እንዲሰጥ ተደርጓል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል። በእነዚህ አካባቢዎች ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የክትባቱ ተደራሽ ማድረግ መቻሉም ተገልጿል።

የክትባት አቅርቦቱ እንደደረሰ ከዚህ በፊት ተደራሽ ባልኾነባቸው እና ተጋላጭ በኾኑ የፍልሰተኞች መጠለያ ጣብያዎች እና የልማት ቀጣናዎች ላይ ለመሥጠት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የመንግሥት ተቋማትም የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩ እና ማኅበረሰቡ ለበሽታው አጋላጭ የኾኑ የተበከለ ውኃን በማከም፣ ምግብን ደግሞ አብስሎ እንዲጠቀም እና የአካባቢና የግል ንጽህናን በአግባቡ መጠበቅ እንደሚገባ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button